በግል አልሚዎች የተገነባ 254 ኪሎ.ዋት ሶላር ሚኒ ግሪድ ተመርቆ ስራ ጀመረ፡፡

 

በነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሠሃረላ አብዱላሂ የተመራ የልዑካን ቡድን በሶማሌ ክልል ፈፋን ዞን ለሸደር ስደተኞች ካንፕ አገልግሎት የሚሰጥ ሂዩማንተሪያን ኢነርጂ ኃ.የተ.የግል ድርጅት ያስገነባው 254 ከሎ.ዋት ሶላር ሚኒግሪድን ግንቦት 12/2016 ዓ.ም መርቀው ስራ አስጀምረዋል፡፡

ሂማን ኢነርጂ ከባለስልጣን መ/ቤቱ በ2015 ዓ.ም አነስተኛ ሶላር ግሪድ ፕሮጀክት ሃይል ማመንጨት፣ማከፋፈልና የኦፕሬሽን ፈቃድ ወስዶ መስራት በጀመረ አጭር ጊዜ ውስጥ ስራውን አጠናቆ ለነዋሪዎቹ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡

በአነስተኛ ግሪድ አልሚዎች የሚሰሩ ፕሮጀክቶች ከግሪድ ርቅው ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ኤሌክትሪክ ሃይል ለማዳረስ በመንግስት ከሚደረገው ጥረት ጎን ለጎን ለፕሮግራሙ ስኬት ያላቸው አስተዋፆ ከፍተኛ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ባለስልጣን መ/ቤቱ ሬጉላተሪ የህግ ማዕቀፎችን ከማዘጋጀት ባለፈ ለፕሮጀክቶቹ ስኬት አስፈላጊውን ትብብር በማድረግና የፕሮጀክቶቹን ሂደት በቅርብ በመከታተል የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ዋና ዳይሬክተር ሠሃረላ አብዱላሂ በምረቃ ስነስርአቱ ላይ ገልፀዋል፡፡

 
  • Hits: 1135

Contact Us

Petroleum and Energy Authority 

P.O.BOX 2554

Tel +251 

FAX +251

Email pea.info@pea.gov.et

Addis Ababa

Ethiopia

Address

Addis Ababa Kadco Group building #2 From 7th to 8th floor. Ethio china Friendship Avenue around Wello sefere.