ኮንትሮባንድ እና ሕገ-ወጥ ንግድ የንግዱ ዘርፍ ዋነኛ ፈተናዎች በመሆናቸው በቅንጅት መታገል እንደሚያስፈልግ ተገለፀ
የካቲት 7 ቀን 2017 ዓ/ም
በቡታጅራ ከተማ በመካሄድ ላይ የሚገኘው የንግድ ጉባኤ ከቀትር በፊት በነበረው ቆይታ የክልል ንግድ ቢሮዎች ፣ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር እና ተጠሪ ተቋማት ስድስት ወር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን ከቀትር በኋላ በቀጠለው ጉባኤ በሪፖርቱ ግምገማ ወጤት የንግድ ዘርፉ ዋነኛ ማነቆ ሕገ-ወጥ አሰራር ነው በጋራ ልንታገለው ይገባል ተብሏል ። የንግድ ዘርፉ ለዘመናት አንቀውት የኖሩ ችግሮችን በአሰራር ማሻሻያዎች ለመቀየር የሚደረገው ጥረትን በዘርፉ ስር ሰደው የቆዩ የተሳሳቱ የንግድ እሳቤዎች በጤናማ የንግድ አውድ ውስጥ ተወዳድሮ ከመስራት ይልቅ ሕገ-ወጥነትን ምርጫ ያደረጉ በመሆናቸው የሚፈልገውን ውጤት ፍጥነት እንደሚገድቡ ተገልጿል ። በሕገወጥ ንግድ ከሚፈተኑ ዘርፎች አንዱ የነዳጅ ግብይት መሆኑ የተገለፀ ሲሆን የፌድራል ተቋማት ከክልሎች ጋር በጋራ በመሆን ስርነቀል ለውጥ ለማምጣት ጉባኤው ወስኖ መውጣት እንዳለበት አቅጣጫ ተሰጥቷል ።
|
- Hits: 1655