የነዳጅ ግብይት ሪፎርም የ2016 የ6 ወር የአፈፃፀም
የታለመ የነዳጅ ድጎማ ውሳኔ ተግባራዊ ከመደረጉ አስቀድሞ በነበሩት ጊዚያት ማለትም በሰኔ ወር 2014 ዓ.ም እስከ 149 ቢሊየን ብር የነበረውና በመጨረሻም በሂደት እስከ 197 ቢሊየን ብር ደርሶ የነበረው ተሰብሳቢ ሂሳብ (ዕዳ)፤ የነዳጅ ዋጋ ማስተካከያ በዋጋ ማረጋጊያ ፈንድ ላይ የሚያስከትለውን እንደምታ በመከታተል በየወሩ እንዲሁም ከመስከረም ወር 2016 ጀምሮ በየ15 ቀኑ ክትትል በመደረጉ እስከ ታህሳስ 30/2023 ድረስ የተሰብሳቢ ዕዳ መጠን ከተጠራቀመው ዕዳ ላይ ተቀናሽ ተደርጎ ወደ ብር 117,493,470,308 ዝቅ እንዲል ማድረግ ተችሏል፡፡ የታለመ ድጎማ አሠራር ተግባራዊ ከተደረገ ጀምሮ እስከ ጥር 19/2016 ድረስ ለ199,358 ተሸከርካሪዎች በጥቅሉ ብር 28,329,028,210.93 ቢሊየን ብር ድጎማ ተደርጓል፡፡ የነዳጅ ግብይትን ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ መንገድ ብቻ እንዲከናወን በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት እስከ ታህሳስ 30 ድረስ በአጠቃላይ ካሉት 1,589 የነዳጅ ማደያዎች ውስጥ በቴሌ ብር የተመዘገቡ 1,550 ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 1,469 ማደያዎች ተግባራዊ ትራንዛክሽን እንዲጀምሩ ተደርጓል፡፡ በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16/2015 ዓ.ም ጀምሮ በክልሎች ደግሞ ከግንቦት 01/2015 ዓ.ም ጀምሮ የነዳጅ ግብይትን ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ ብቻ እንዲከናወን በመደረጉ እስከታህሳስ 30/2016 ዓ.ም ድረስ 155,422,750,311 ብር ነዳጅ በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ ግብይት እንዲፈፀም በማድረግ የቁጥጥር ስርዓቱን በዲጂታል ዘዴ መደገፍ ተችሏል፡፡ |
- Hits: 733