የነዳጀ ሪፎርም አፈፃፀም ከክልል አስፈፃሚ አካላት ጋር በጋራ ተገመገመ።
ላለፉት ስድስት ወራት ከተሰሩ የቁጥጥርና ክትትል ስራ ግኝቶች መነሻነት የነዳጅ ሪፎርም አፈፃፀም ሪፖርት የክልል ንግድ ቢሮ ሃላፊዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በጋራ ተገምግሟል። በጋራ የግምገማ መድረኩ ላይ በዋነኝነት በክልሎች የነዳጅ ግብይ ሂደት ላይ የሚስተዋሉ ሕገወጥ ተግባራት፣ዲጂታል ነዳጅ ግብይት አፈፃፀም እና የነዳጅ አቅርቦት ሠንሠለት ስርአት አተገባበር የተመለከቱ ርዕሰ ጉዳዮች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል። የነዳጅ ሪፎርም አተገባበርን በተመለከተ በሪፎርሙ የተቀመጡ ግቦችን በአብዛኛው መሳካታቸው በተሳታፊዎች የተገለፀ ሲሆን በስድስት ወር የክትትል ሪፖርቱ የተገለፁ የአፈፃፀም ክፍተቶችን በተመለከት ከየክልሉ ነባራዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ በተደረገ ግምገማ በክፍተት ከተነሱ ጉዳዬች መካከል ዲጅታል ግብይትን በተመለከተ አንዳንድ አከባቢዎች ላይ በካሽ የመሽጥ ሁኔታዎች መኖራቸው፣ ለእርሻና ለተለያዩ አገልግሎቶች ነዳጅ በበርሜል እና በጀሪካን የመቅዳት ፈቃድ አሰጣጥ ላይ ያሉ የአሰራር ክፍተቶች መኖራቸው ተገልፆ በቀጣይ የአሰራር ማሻሻያዎች ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ተጠቁሟል። ከዲጂታል ነዳጅ ግብይት ጋር ተያይዞ የሚነሳ የኔትዎርክ ችግር ከኢትዮ ቴሌኮም በኩል በተሰጠ ምላሸ ችግሩን እንደ ዋነኛ ምክንያት ማቅረብ ተገቢ አለመሆኑ ተገልፆ የኔትዎርክ ችግር ያለበት አከባቢ ካለ ቦታው በግልዕ ተጠቅሶ መቅረብ እንዳለበት የተነገረ ሲሆን ችግሩ ካለ አፋጣኝ የማሻሻያ ስራዎች ለመስራት ዝግጁነት መኖሩ ተመላክቷል። |
- Hits: 1005