አይሻ የንፋስ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በባለስልጣን መ/ቤቱ የበላይ ኃላፊዎች ተጎበኘ፡፡

 

አይሻ ¦¦ 120 ሜጋ ዋት የንፋስ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የትግበራ ሂደት በባለስልጣን መ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሣሀረላ አብዱላሂ ፣ በኢነርጂ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አህመድ ሰኢድ እና በፈቃድና ቴክኒካል ሬጉሌሽን ዳይሬክተር አቶ ባህሩ ኦልጂራ ተጎብኝቷል፡፡

እስካሁን ባለው የፕሮጀክት አፈፃፀም የፍተሸና የሙከራ ስራ በማጠናቀቅ ሁለት ክላስተሮች ወደ ብሔራዊ የኤሌክትሪክ ቋት በማስገባት 40 ሜጋ ዋት ያህል ሃይል ማመንጨት አቅም ያላቸው 16 ተርባይኖች ሃይል ማመንጨት መጀመራቸውን በጉብኝቱ ወቅት ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ በፕሮጀክት ሳይቱ በመገኘት ለመመልከት እንደተቻለው ሶስተኛና አራተኛ ክላስተር የንፋስ ተርባይኖች የሙከራና ፍተሸ ስራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

ከፕሮጀክት ወጪ ጋር በተያያዘ ያሉ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት 257,285,160.00 ዶላር ሲሆን በመንግስት 38,592,774.00 ዶላር በብር የተከፈለ ሲሆን 218,692,386.00 ዶላር ከቻይና ኤግዚም ባንክ በየጊዜው ለሚሰሩ ስራወዎች የሚከፈል መሆኑን ከፕሮጀክት አፈፃፀም ሪፖርቱ ያሳያል፡፡

ይህን በተመለከተ በመ/ቤቱ የፈቃድና ቴክኒካል ሬጉሌሽን ስራ አስፈፃሚ አቶ ባህሩ ኦልጂራ መሰል ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ በማጠናቀቅ ለሚፈለገው ዓላማ ግልጋሎት እንዲሰጡ ለማስቻል የቅርብ ክትትል እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡

በአጠቃላይ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ እያንዳንዳቸው 2.5 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጨት አቅም ያለቸው 48 ተርባይኖችን በመትከል 120 ሜጋ ዋት ሃይል ያመነጫል ተብሎ ይታሰባል፡፡ የአይሻ ¦¦ የንፋስ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከባለስልጣን መ/ቤቱ ጥር 18/2008 በተሰጠ ኢንቨስትመንት ፈቃድ ትግበራው የተጀመረ ሲሆን አስካሁን ያለው አጠቃላይ የፕሮጀክት አፈፃፀም ከ83 በመቶ በላይ መድረሱን በሪፖርትና በተደረገ ምልከታ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡

 
  • Hits: 1125

Contact Us

Petroleum and Energy Authority 

P.O.BOX 2554

Tel +251 

FAX +251

Email pea.info@pea.gov.et

Addis Ababa

Ethiopia

Address

Addis Ababa Kadco Group building #2 From 7th to 8th floor. Ethio china Friendship Avenue around Wello sefere.