የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎች የሃይል መሙያ ማዕከላትን ማስፋፋት ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚያስፈልግ ተገለፀ፡፡

 
የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ከአረንጓዴ ኢኮኖሚ ስትራቴጂ ጋር ያለውን ቁርኝት በተመለከተ የዘርፉ ተዋኒያን በተገኙበት ነሃሴ 21/2016 ዓ.ም በሃይሌ ግራንድ ሆቴል የፓናል ውይይት ተካሄደ፡፡
በዕለቱ የፓናል ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሠሀርላ አብዱላሂ በአሁኑ ወቅት ለህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎች በሀገር ውስጥ አገልግሎት ላይ እየዋሉ ከመምጣታቸው ጋር በተገናኘ ለህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ የሃይል መሙሊያ ማዕከላትን በብዛት እንዲኖሩ ማድረግ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡
ከዚሁ ጋር በተገናኘ የሃይል መሙያ ማዕከላቱ የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት፣ታሪፍ እና ከማዕከላቱ ግንባታ ጋር በተያያዘ ሊኖር ሰለሚገባ ስታንዳርድ የሕግ ማዕቀፍ እየተዘጋጀ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ከትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አቶ ይዘንጋው ይታይህ (ዶ/ር) የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎች ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ባላቸው አስተዋዕፆ ከቀረፅ ነፃ እንዲገቡ የተደረገበት አሰራር መኖሩን ገልፀዋል፡፡
በመጨረሻም ዋና ዳይሬክተር ሠሀርላ እንደገለፁት የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎች ለአከባቢ ጥበቃና አረንጓዴ ኢኮኖሚ ግናባታ ካላቸው አበርክቶ ባሻገር ሀገራችን ለነዳጅ የምታወጣውን ወጪ ለመቀነስም እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡
 
  • Hits: 1115

Contact Us

Petroleum and Energy Authority 

P.O.BOX 2554

Tel +251 

FAX +251

Email pea.info@pea.gov.et

Addis Ababa

Ethiopia

Address

Addis Ababa Kadco Group building #2 From 7th to 8th floor. Ethio china Friendship Avenue around Wello sefere.