በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የንግድና ቱሪዝም ቋሚ ኮሚቴ በባለስልጣን መ/ቤቱ እየተከናወኑ ባሉ ሥራዎች ላይ ከተቋሙ የበላይ አመራሮች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡
በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የንግድና ቱሪዝም ቋሚ ኮሚቴ በባለስልጣን መ/ቤቱ እየተከናወኑ ባሉ ሥራዎች ላይ ከተቋሙ የበላይ አመራሮች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡ ከውይይቱ በኋላም የነዳጅ አቅርቦት ሂደት መከታተያ ሥርዓት (Fuel Supply Chain Management System) የተመለከተ ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡
|
- Hits: 2306
በነዳጅ ዘርፉ የሚስተዋል ሕገ-ወጥነትን ለመከላከል የነዳጅ ኩባኒያዎች በስራቸው ከሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች ጋር ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡
አዲስ አባበ፤የካቲት27/2017 (ነ.ኢ.ባ)
በነዳጅ ዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት የነዳጅ አከፋፋይ ኩባኒያዎች በስራቸው ከሚገኙ ማደያዎች ጋር ተወያይተው ሪፖርት እንዲያደርጉ በተሰጠው አቅጣጫ መሠረት ኩባኒያዎቹ ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ በዚሁ መሠረት በዛሬው ዕለት ኦላ ኢነርጂ ኢትዮጵያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባኒያ በስሩ ከሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎች ጋር ውይይት አድርጓል፡፡
የኩባኒያው ጀነራል ማናጀር የሱፍ ኢልሃሚሊ በውይይቱ ላይ በመገኘት ባደረጉት ንግግር በኩባኒያው ስር የሚገኙ ሁሉም ማደያዎች የሀገሪቱ የቁጥጥር ሕግ በሚያዘው መሠረት ስራቸውን እንዲሰሩ እና ንፁህ፤ጥራት ያለውና አስተማማኝ አገልግሎት በመስጠት ኩባኒያው የገነባውን ብራንድና ስም የማስጠበቅ ኃላፊነት እንዳለባቸው በማሳሳብ በኩባኒያው በኩል አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ገልፀዋል፡፡ ለዚህም ማሳሰቢያ ተግባራዊነት ሁሉንም ማደያዎች ቃል እንዲገቡ አድረገዋል፡፡
በውይይቱ ላይ ተገኝተው ማብራሪያ የሰጡት የባለስልጣን መ/ቤቱ የነዳጅ ዘርፍ ኃላፊና ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዲባራ ፉፋ እንደገለፁት የነዳጅ ግብይት ላይ የሚስተዋሉት ሕገ-ወጥ ተግባራት ዕለት ዕለት መልካቸውን እየቀያየሩና እየተባባሱ የመጡ በመሆኑ ህብረተሰቡን የኑሮ ጫና እንዲሸከም በማድረግ ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡ በነዳጅ ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ቀጥታ ህብረተሰብ ላይ የሚፈፀሙ በደሎች በመሆናቸው ሁሉም በኃላፊነት ስሜት ከችግሩ ለመውጣት የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንደሚገባው አሳስበው ወደ እርምጃ ከመገባቱ በፊት ውይይትን ማስቀደም እና መፍትሄ መስጠት ላይ ለማተኮር ሲባል እንደዚህ አይነት ውይይቶች እንዲደረጉ ቅድሚያ ተሰጥቷል ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል፡፡
በማደያዎቹ በኩልም ከነዳጅ አቅርቦት ፍትሃዊነት፣ዲጂታል ግብይት ላይ የሕብረተሰቡ ግንዛቤ አነስተኛ መሆንና ተባባሪ አለመሆን እና በጀሪካን እና በርሜል ሽያጭ እንድንፈፅም በደብዳቤ የምንታዘዝ በመሆኑ በኛም ስራ ላይ በበርሜል ተቀድተው በከፍተኛ ዋጋ በሕገወጥ የሚቸረቸር ነዳጅ የአቅርቦት ችግር እየፈጠረብን ነው ብለዋል፡፡
በኩባኒያው ኦፕሬሽን ዳይሬክተር አቶ ኃይሉ በሰጡት አቅጣጫ ሁሉም ማደያዎች ሽያጫቸውን ሙሉ በሙሉ በዲጂታል ማድረግ እንደሚገባቸው ከማንኛውም ሕገ-ወጥ ተግባር ራሳቸውን መጠበቅ እንደሚገባ እና የማሽን ብልሽትን በወቅቱ ማሳወቅና ማስጠገን እንደሚገባ የነዳጅ ትዕዛዝን በተመለከተ የማንም ጣልቃ-ገብነት ሳይኖር ከፍለው ባዘዙት መሠረት እንደሚቀርብ አረጋግጠዋል፡፡
|
- Hits: 2103
የህዝብን ጥቅም ያስቀደመ ፍትሃዊ የነዳጅ አቅርቦት፣ስርጭትና ግብይት እንዲሰፍን ትኩረት ሰጥተን እንሠራለን፡፡
የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት በቢሾፍቱ ከተማ ከነዳጅ አከፋፋይ ኩባኒያዎች ጋር የነዳጅ ገበያ ድርሻ ውሳኔን በተመለከተ በተደረገ ውይይት ላይ “ከፍተኛ የሀገር ሀብት ፈሶበት ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባ ነዳጅ የህዝብን ጥቅም ባስቀደመ ፍትሃዊ፣ሕግን ያከበረ የአቅርቦት፣ስርጭትና የግብይት ስርዓት እንዲኖር ለማድረግ ሚንስቴር መ/ቤቱ በዘርፉ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ጥብቅ ክትትል ያደርግበታል” በማለት አጽእኖት ሰጥተው ገልፀዋል፡፡
ከነዳጅ ስርጭትና ግብይት ጋር ተያይዞ ከፍተኛ ሕገ-ወጥነት እንደሚስተዋል የተናገሩት ሚኒስትሩ ይህን ተከትሎ ማደያዎችን በማድረቅ የነዳጅ አቅርቦት ችግር እንዳለ ለማስመሰል በሚደረገው ጥረት ላይ ጠበቅ ያለ እርምጃ መውሰድ የሚያስችል የአሰራር ስርዓት እየተዘረጋ መሆኑን አመላክተው ሕገወጥነቱ በሚፈጥራቸው ሰውሰራሽ እጥረቶች በሚፈጥረው ተፅዕኖ ምክንያት ከሌለ ሀብት ላይ ከፍተኛ በጀት ተመድቦ ነዳጅ የመጨመር ፍላጎት እንደማይኖር ተናግረዋል፡፡ የገበያ ድርሻ ድልድሉንም በተመለከተ በየሶስት ወሩ ወቅታዊ ሁኔታዎችን ባገናዘበ መልኩ የሚከለስ ሲሆን የሁሉንም ሀሳብ በእኩልነት ተመልክተን ፍትሃዊ ክፍፍል እንዲኖር እናደርጋለን ብለዋል፡፡
|
- Hits: 1885
የነዳጅ ግብይት ረቂቅ አዋጅ መፅደቅ በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ፡፡
የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ክህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ንግድና ቱሪዝም ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጋር በነዳጅ ግብይት ረቂቅ አዋጅ ላይ በዛሬው ዕለት ባደረጉት ውይይት፤ የረቂቅ አዋጁ መፅደቅ በነዳጅ ግብይት ላይ የሚስተዋሉ ሕገ-ወጥ ተግባራትን ለመቆጣጠር ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የቋሚ ኮሚቴው አባላት በውይይቱ ላይ በነበራቸው ቆይታ፤ በአዋጁ አስፈላጊነት እና ቀደም ሲል ይሰራበት የነበረው የነዳጅና የነዳጅ ውጤቶች አቅርቦት ሥራን ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ 838/2006 መተካት ያስፈለገበት ዋናኛ ምክንያት እና በአዋጁ ይዘት ላይ ማብራሪያ የጠየቁ ሲሆን በረቂቅ አዋጁ ይዘት ላይም አስተያየት ሰጥተዋል፡፡
ባለስልጣን መ/ቤቱ ከአባላቱ በቀረቡለት ጥያቄዎች ላይ ሰፊ ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን በዋነኝነት ረቂቅ አዋጁን ማዘጋጀት ያስፈለገበት ምክንያት ቀደም ሲል በነበረው አዋጅ ያልተካተቱ ወሳኝ ጉዳዮች መኖራቸው፣ የቀደመው አዋጅ አቅርቦት ላይ ትኩረት የሚያደርግና ስርጭትን ግብይትን የተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ክፍተት ያለው መሆኑ፣ የቁጥጥር ስራውን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ የተደረጉ የአሰራር ስልቶችን ያማያካትትና ወቅታዊ ባለመሆኑ እና በተለይ በግብይት ላይ የሚስተዋሉ ሕገ-ወጥነት ላይ ጠበቅ ያለ እርምጃ መውሰድ ያማያስችል በመሆኑ ነው የሚል ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡
በውይይቱ ማጠቃለያ የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ክብርት ወ/ሮ አሻ ያህያ የአዋጁ ወቅታዊነት እና አስፈላጊነት በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት ያማያጠያይቅ ጉዳይ መሆኑን ገልፀው ቋሚ ኮሚቴው ከባለስልጣን መ/ቤቱ ከተሰጠው ማብራሪያ በተጨማሪ በቀጣይ በትኩረት የሚመለከተው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
|
- Hits: 2006
ከከፍተኛ ኤሌክትሪክ ሃይል ተጠቃሚ ፋብሪካዎች ጋር ኢነርጂ አስተዳደር ፈቃደኝነት ስምምነት ተፈረመ።
ጥር 24/2017 (ነ.ኢ.ባ) ከሶስት ከፍተኛ ኤሌክትሪክ ሃይል ተጠቃሚ ፋብሪካዎች፤ ድሬደዋ ምግብ ኮምፕሌክስ፣ ቱሬ ሲሚንቶ ፋብሪካ እና ሂይኒከን ኢትዮጵያ ስር ከሚገኘው ሀረር ቢራ ፋብሪካ ጋር የፈቃደኝነት ኢነርጂ አስተዳደር ስምምነት (Voluntary energy management agreement) ባለስልጣን መ/ቤቱ ተፈራረመ፡፡ በባለስልጣን መ/ቤቱና በፋብሪካዎቹ መካከል የተፈፀመው ስምምነት ፋብሪካዎቹ በምርት ሂደት የሚጠቀሙትን ኢነርጂ ምርትን ሣይቀንሱ በተለያዩ ምክንያቶች የሚያጋጥም የኤሌክትሪክ ሃይል ብክነትን ለመቀነስ የሚያስችላቸውን እርምጃዎች ለማከናወን ሲሆን በባለስልጣን መ/ቤቱ በኩል ይህን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችላቸውን ድጋፍና ክትትል ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት ነው፡፡ ከስምምነቱ ሠነድ ለመረዳት እንደተሞከረው የስምምነት ሂደቱ የሚጀምረው ፋብሪካዎቹ እየተጠቀሙ ያሉትን ኢነርጂ ኦዲት በማስደረግ የሚባክን ኢነርጂ መጠንን በማወቅ በሂደት የማሻሻያ ሥራዎችን ለመስራትና ብክነቱን ለመቀነስ ዕቅድ አስቀምጠው የሚተገብሩት ሲሆን ባለስልጣን መ/ቤቱ የዕቅዱን ሂደት በመከታተል እና የሚያስፈልጉ ድጋፎችን በመስጠት ውሉ የሚፈፀም ይሆናል፡፡ ባለስለጣኑን ወክለው ስምምነቱን የፈረሙት የኢነርጂ ብቃትና ቁጠባ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዘውገ ወርቁ እንደገለጹት በከፍተኛ ሃይል ተጠቃሚ ኢንደስትሪዎች ላይ የሚባክን ኢነርጂን መቀነስ እንደ ሀገር የሚባክን ኢነርጂን ለመቀነስ እንደሚያስችል፣በኤሌክትሪክ መስመሮች ላይ የሚያጋጥም መጫናነቅና የሃይል መቆራረጥን እንደሚቀነስ ብሎም አለአግባብ የሚጨምር የኢነርጅ ፍላጎትን በመቀነስ ኤሌክትሪክ ሃይል ለሚፈለግባቸው አከባቢዎች ማድርስ እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡ ጨምረውም እንደገለጹት ኢንደስትሪዎች የሚጠቀሙትን ኢነርጂ ከብክነት በመከላከል የኤሌክትሪክ ክፍያቸውን መቀነስ እንደሚያስችላቸውና በኢነደስትሪ ውስጥ ዘላቂና ተወዳዳሪ ሆነው እንዲቀጥሉ የሚያስችል አቅም እንደሚፈጥር ገልፀዋል፡፡ በቀጣይም ከሌሎች ኢንደስትሪዎች ጋር ስምምነቱ እንደሚፈፀም እና ስምምነቱን ከፈረሙት ጋር ደግሞ የክትትልና ድጋፍ ሥራ የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል፡፡ ባለስልጣን መ/ቤቱ ባስለፍነው ሳምንት ስምምነቱን ከተፈራራመቸው ሶስት ፋብሪካዎች በተጨማሪ ከዚህ ቀደም ስምምነት ካደረገው ናሽናል ሲሚንቶ ሼር ካንፓኒ ስምምነቱን ተከትሎ የተተገበሩ ስራዎች ላይ ክትትልና በቀጣይ ሊደረጉ በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡ |
- Hits: 2155
More Articles ...
Page 2 of 6