ኢነርጂ አስተዳደር ስርዓት ደረጃ (Energy Management System Standard) ስልጠና በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡

 
ኢነርጂ አስተዳደር ስርዓት ደረጃ (Energy Management System Standard) በተመለከተ ለከፍተኛ ኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ኢንዱስትሪ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ለተከታታይ አምስት ቀናት የሚሰጠው ስልጠና በዛሬው ዕለት በአዳማ ከተማ በይፋ ተጀምሯል፡፡
የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን የኢነርጂ ብቃት ማረጋገጥና ቁጠባ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ዘውገ ወርቁ በስልጠና መርሀግብሩ ማስጀመሪያ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የኢነርጂ ማኔጅመንት ሲስተም ስታንዳርድ የኃይል አጠቃቀምን በማሻሻል የተሻለ ትርፍና ዘለቄታዊ የኃይል ደህንነት እንዲኖር እንዲሁም ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ጠቅሰዋል።
ስልጠናው የሚኖረው ፋይዳን በተመለከተ የኢነርጂ ማኔጅመንት ሲስተም ስታንዳርድ በመጠቀም የኃይል ብክነትን በማስቀረት የኤሌክትሪክ ፍጆታ ክፍያን መቀነስና ተወዳዳሪ ኢኮኖሚ ለመፍጠር፤ እንዲሁም የካርበን ዳይ ኦካሳይድ ልቀትን በመቀነስ አካበቢያዊ ብክለትን ለመከላከል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ገለጸዋል።
የኢነርጂ ማኔጅመንት ሲስተም ስታንዳርድ አተገባበርን በተመለከተ በአገሪቱ ውስጥ ያሉ ከፍተኛ ሃይል ተጠቃሚ ኢንዱስትሪዎች ላይ ኢነርጂ ኦዲትን ተግባራዊ በማድረግ ፍጆታቸውን ማወቅ እና ያለአግባብ የሚባክን ኢነርጂን በብቃትና ቁጠባ ላይ የተመሠረተ አጠቃቀም እንዲኖር በማስቻል የኢነርጂ ፍጆታን ማሻሻል ይቻላል ብለዋል ፡፡
የኢነርጂ ኦዲት መረጃን መሠረት በማድረግ በቂ ክትትል፤ ድጋፍና የኢነርጂ አጠቃቀም ትንታኔና በቴኒካል ድጋፍ ክፍተት ዙሪያ ያሉትን ችግሮች ለማሻሸል ከሚኖረው ከፍኛ አስተዋእፆ በተጨማሪ ዋጋን መሠረት በማድረግ የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ትንታኔ የመስጠት ሂደትን የሚያካትት ነው በማለት አብራርተዋል፡፡
በመጨረሻም ከፍተኛ ኃይል ተጠቃሚ ኢንዱስትሪዎች የኢነርጂ ማኔጅመንት ሲስተም ስታንዳርድን ተግባራዊ በማድረግ የኢነርጂ አጠቃቀም ብቃትና ቁጠባ እንደ ቁልፍ ስራ በመተግበር በተለይም የኢነርጂ ኦዲት አገልግሎትን በመጠቀም ሁሉም ሰልጣኞች የወሰዱትን ስልጠና ተግባራዊ በማድረግ የኢነርጂ ልማት ክፍለ-ኢኮኖሚው ላይ ትልቅ እምርታዊ ለውጥ ማምጣት እንደያስሚያስችል አስገንዝበዋል፡፡
 
  • Hits: 790

Contact Us

Petroleum and Energy Authority 

P.O.BOX 2554

Tel +251 

FAX +251

Email pea.info@pea.gov.et

Addis Ababa

Ethiopia

Address

Addis Ababa Kadco Group building #2 From 7th to 8th floor. Ethio china Friendship Avenue around Wello sefere.