ለትግራይ ክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ለኤሌክትሪክ ኢንስታሌሽን ብቃት ማረጋገጥ የተግባር መፈተኛ አገልግሎት የሚሆኑ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ድጋፍ ተበርክቷል፡፡

 

ለትግራይ ክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ለኤሌክትሪክ ኢንስታሌሽን ብቃት ማረጋገጥ የተግባር መፈተኛ አገልግሎት የሚሆኑ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ድጋፍ ተበርክቷል፡፡

የተግባር መፈተኛ ቁሳቁሶቹ የተበረከቱት በነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን የክልል ኦፕሬሽን ማስተባበሪያ ዳሬክቶሬት በኩል ሲሆን በክልሉ ውኃና ኢነርጂ ቢሮ በመገኘት የክልል ስራዎች አስተባበሪ አቶ በላይነህ ግዛው ዕቃዎቹን አስረክበዋል፡፡ 

በባለስልጣን መ/ቤቱ የሚደረጉ መሰል የአቅም ግንባታ እና የቁሳቁስ ድጋፎች ለክልሉ በውክልና የተሰጡ ስራዎችን ለማከናወን የሚያስችሉ ናቸው፡፡ የውክልና ስራው በነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን እና በክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮ መካከል በተደረገ ስምምነት መሠረት  በባለስልጣኑ ከሚሰጡ አገልግሎቶች የተወሰኑት በክልሉ እንዲሰጡ በ2009 ዓ.ም ከስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ ይህንን ስምምነት መሠረት በማድረግ በክልሉ እንዲሰጡ ከተወሰኑ ስራዎች መካከል የኤሌክትሪክ መሰመር ዝርጋታ ባለሙያዎች የሙያ ብቃት ማረጋገጥ ደረጃ 4 የብቃት ማረጋገጫ ዘርፍ አንዱ ሲሆን ይህንን ስራ ተግባራዊ ለማድረግ ሚያስችል የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ድጋፉ ስራውን በቀጣይነት ለማሰራት የሚያስችል አቅም ይፈጥራል ተብሎ ይታሰባል::

 
  • Hits: 969

Contact Us

Petroleum and Energy Authority 

P.O.BOX 2554

Tel +251 

FAX +251

Email pea.info@pea.gov.et

Addis Ababa

Ethiopia

Address

Addis Ababa Kadco Group building #2 From 7th to 8th floor. Ethio china Friendship Avenue around Wello sefere.