በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድና ቱሪዝም ቋሚ ኮሚቴ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተገጠመለትን የነዳጅ ማደያ ጎበኙ፡፡

 

 
 
መጋቢት 30/2017 ዓ.ም
 
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድና ቱሪዝም ቋሚ ኮሚቴ ሲ.ኤ.ሚ.ሲ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ የሚገኘውንና smart fuel station ትግበራ አካል ሆኖ የሙከራ ስራ ከጀመረ አንድ ዓመት ያስቆጠረውን የተባበሩት የነዳጅ ማደያን ጎብኝተዋል፡፡ በጉብኝቱ ላይ የባለስልጣን መ/ቤቱ የበላይ አመራሮች፣ የኢትዮቴሌኮምና በአጋርነት ሲስተሙን እያበለጸገ ያለው ድርጅት ባለሙያዎች ለቋሚ ኮሚቴው ሙያዊ ማብራሪያ የሠጡ ሲሆን በተግባር እየተሠሩ ያሉ ሥራዎችንም አስጎብኝተዋል፡፡
 
የነዳጅ ማደያዎችን ወደ smart fuel station ለመቀየር በሁለት የነዳጅ ማደያዎች ላይ የተጀመረው የሙከራ ስራ የቁጥጥር ስራውን በቀጣይነት ከፍ ባለ ደረጃ ለመስራት በቴክኖሎጂ በመታገዝ ለማዘመን ከሚደረጉ ጥረቶች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ Smart fuel station ሙከራ ስራ እስካሁን እየተተገበሩ ያሉ ስርዓቶችን ክፍተት የሚሞላ እና ሙሉ ለሙሉ በነዳጅ ግብይት ላይ የሚፈጸሙ ሕገ-ወጥ ተግባራትን መከላከል የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡ በዚህም በነዳጅ መቅጃ ማሽኖች ላይ የሚፈፀም ቅሸባን፣ በታንከር ውስጥ የተራገፈ ነዳጅ ተሸጦ ሳያልቅ ነዳጅ የለም የሚባለውን ሁኔታ የሚያስቆም፣ ትክክለኛ የነዳጅ ርክክብና ሽያጭ መጠንን በፍሎ ሜትር በመለካት የሚያሳውቅ፣ ነዳጅ የጫኑ ተሸከርካሪዎች ምክንያታቸውን ባላሳወቁበት ሁኔታ አቅጣጫ ለመቀየር ሲሞክሩ ማስቆም የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎች የተገጠመለትና ለቁጥጥር አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን የሚሰጥ አላስፈላጊ የማጭበርበር ሙከራዎች ሲኖሩም በራሱ ምላሽ እንዲሰጥ ሆኖ የተሠራ ነው፡፡
 
በአሁኑ ወቅት በነዳጅ ግብይት ላይ የሚስተዋሉ ሕገ-ወጥ ተግባራትን ለመቆጣጠር የተለያዩ ቴክኖሎጂዎች ተግባራዊ እየተደረጉ የሚገኙ ሲሆን ከነዚህ መካከል አንደኛው Fuel supply chain management system ነው፡፡ በዚህ መተግበሪያ ነዳጅ ትዕዛዝ ከተሰጠበት ጊዜ አንስቶ ነዳጁ የታዘዘበት ማደያ እስከሚደርስ የሚካሄዱ ሂደቶችን በቀጥታ በሲስተም አማካኝነት መከታተል የሚያስችል ስርዓት ነው፡፡ ሌላኛው ደግሞ ተሸከርካሪዎች የያዙትን ጭነት በተቀመጠላቸው ጊዜ ገደብ ወደ መዳረሻው እንዲያደርሱ በተገጠመላቸው ጂ.ፒ.ኤስ የሚደረግ ቁጥጥር ሲሆን በተጨማሪም የዲጂታል ነዳጅ ሽያጭ መቆጣጠሪያ ስልት ሆነው እየተሠራባቸው የሚገኙ ናቸው፡፡

 

 
 

 

 
  • Hits: 2437

Contact Us

Petroleum and Energy Authority 

P.O.BOX 2554

Tel +251 

FAX +251

Email pea.info@pea.gov.et

Addis Ababa

Ethiopia

Address

Addis Ababa Kadco Group building #2 From 7th to 8th floor. Ethio china Friendship Avenue around Wello sefere.