በነደጅ ውጤቶች ዋጋ ግንባታና የትርፍ ህዳግ አሠራር በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡

 

አዳማ፤ መጋቢት 10/2017 ዓ.ም /ነ.ኢ.ባ/፡-

በነዳጅ ውጤቶች ዋጋ ግንባታና የትርፍ ህዳግ አሠራር በተመለከተ የባለስልጣኑን ባለሙያዎች ጨምሮ ከኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት እና ለንግድ ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ለተውጣጡ ባለሙያዎች ስልጠና በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡ የነዳጅና ኢነርጂ ገበያ ጥናትና ታሪፍ ስራ አስፈፃሚ አቶ ለሜሳ ቱሉ ለሰልጣኞች ባስተላለፉት መልዕክት ነዳጅ ኢኮኖሚያዊና ስትራቴጂክ ምርት በመሆኑ የነዳጅ አቅርቦትና ስርጭትን አስተማማኝነትና ፍታሀዊነት ለመረጋገጥ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ዘመናዊና ግልፅነት ያለው የነዳጅ ግብይት ሥርዓት መገንባት የነዳጅ ተጠቃሚዎችና የአገልግሎት ሰጪዎች መብትና ግዴታን ለማስከበር ትልቅ ሚና እንዳለው አብራርተዋል፡፡

የግብይት ሥርዓት ሲባል ነዳጅ ለተጠቃሚዎች ሲቀርብ በሚደረግ የጥራት ቁጥጥር፣ በጅምላና ለችርቻሮ ማከፋፈል እንዲሁም የትርፍህዳግ ፤የታሪፍና ዋጋ ግንባታ አሠራር የግብይት ተዋንያን የፈቃድ አሰጣጥ መካለከል የሚኖረውን የግንኙነት አግባብ የሚመራበት የተገደበ የግብይት ሥርዓት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም በነዳጅ ግብይት የእሴት ሰንሰለት ትንተና ውስጥ የተለዩ ቁልፍ የዘርፉ ችግሮች መካከል ዋና ዋናዎቹ ነዳጅ ዋጋ፤ የታሪፍና የትርፍ ህዳግ የአሠራር ክፍተት የግብይት መሠረተ ልማት የሎጂስቲክ ውስንነት እንዲሁም የአደረጃጅት የአመራር የአሰራር የክትትልና ቁጥጥር ሥርዓት ክፍተት እንደነበረ ገልፀዋል፡፡

እነዚህን ችግሮች ለመፍታት በነዳጅ ሪፎርም ትግበራ ወቅት በተከነውኑ ትግባራት ከተገኙ ውጤቶች ውስጥ አንዱ የነዳጅ ዋጋና የትርፍ ህዳግ አስተዳደር ጋር የተያያዘ ሲሆን በዚህም በኪሳራ ሲሸጥ የነበረው ነዳጅ በጥናት ላይ የተመሠረተ ተከታታይ የዋጋ ማስተካከያ በማድረግ የሀገር ውስጥ ዋጋው የዓለም ዋጋ ጋር ተቀራራቢ እንዲሆን ከማድረግ በተጨማሪም የነዳጅ ዱቤ ሽያጭ በማስቀረት መቶ በመቶ እጅ በእጅ ሽያጭ እንዲሆን እና የነዳጅ የትራንዚት ቁጥጥር እንዲኖር እንዲሁም የነዳጅ አዳዮች የተሻለ የትርፍ ህዳግ እንዲያገኙ ምቹ ሁኔታ ከፈጠረው አንዱ የነዳጅ ሪፎርም ትግበራት መሆኑን ስራ አስፈጻሚው ጠቅሰዋል፡፡

 
  • Hits: 1479

Contact Us

Petroleum and Energy Authority 

P.O.BOX 2554

Tel +251 

FAX +251

Email pea.info@pea.gov.et

Addis Ababa

Ethiopia

Address

Addis Ababa Kadco Group building #2 From 7th to 8th floor. Ethio china Friendship Avenue around Wello sefere.