የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎች የሃይል መሙያ ማዕከላትን ማስፋፋት ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚያስፈልግ ተገለፀ፡፡
የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ከአረንጓዴ ኢኮኖሚ ስትራቴጂ ጋር ያለውን ቁርኝት በተመለከተ የዘርፉ ተዋኒያን በተገኙበት ነሃሴ 21/2016 ዓ.ም በሃይሌ ግራንድ ሆቴል የፓናል ውይይት ተካሄደ፡፡
በዕለቱ የፓናል ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሠሀርላ አብዱላሂ በአሁኑ ወቅት ለህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎች በሀገር ውስጥ አገልግሎት ላይ እየዋሉ ከመምጣታቸው ጋር በተገናኘ ለህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ የሃይል መሙሊያ ማዕከላትን በብዛት እንዲኖሩ ማድረግ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡
ከዚሁ ጋር በተገናኘ የሃይል መሙያ ማዕከላቱ የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት፣ታሪፍ እና ከማዕከላቱ ግንባታ ጋር በተያያዘ ሊኖር ሰለሚገባ ስታንዳርድ የሕግ ማዕቀፍ እየተዘጋጀ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ከትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አቶ ይዘንጋው ይታይህ (ዶ/ር) የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎች ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ባላቸው አስተዋዕፆ ከቀረፅ ነፃ እንዲገቡ የተደረገበት አሰራር መኖሩን ገልፀዋል፡፡
በመጨረሻም ዋና ዳይሬክተር ሠሀርላ እንደገለፁት የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎች ለአከባቢ ጥበቃና አረንጓዴ ኢኮኖሚ ግናባታ ካላቸው አበርክቶ ባሻገር ሀገራችን ለነዳጅ የምታወጣውን ወጪ ለመቀነስም እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡
|
- Hits: 1107
ለትግራይ ክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ለኤሌክትሪክ ኢንስታሌሽን ብቃት ማረጋገጥ የተግባር መፈተኛ አገልግሎት የሚሆኑ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ድጋፍ ተበርክቷል፡፡
ለትግራይ ክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ለኤሌክትሪክ ኢንስታሌሽን ብቃት ማረጋገጥ የተግባር መፈተኛ አገልግሎት የሚሆኑ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ድጋፍ ተበርክቷል፡፡ የተግባር መፈተኛ ቁሳቁሶቹ የተበረከቱት በነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን የክልል ኦፕሬሽን ማስተባበሪያ ዳሬክቶሬት በኩል ሲሆን በክልሉ ውኃና ኢነርጂ ቢሮ በመገኘት የክልል ስራዎች አስተባበሪ አቶ በላይነህ ግዛው ዕቃዎቹን አስረክበዋል፡፡ በባለስልጣን መ/ቤቱ የሚደረጉ መሰል የአቅም ግንባታ እና የቁሳቁስ ድጋፎች ለክልሉ በውክልና የተሰጡ ስራዎችን ለማከናወን የሚያስችሉ ናቸው፡፡ የውክልና ስራው በነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን እና በክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮ መካከል በተደረገ ስምምነት መሠረት በባለስልጣኑ ከሚሰጡ አገልግሎቶች የተወሰኑት በክልሉ እንዲሰጡ በ2009 ዓ.ም ከስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ ይህንን ስምምነት መሠረት በማድረግ በክልሉ እንዲሰጡ ከተወሰኑ ስራዎች መካከል የኤሌክትሪክ መሰመር ዝርጋታ ባለሙያዎች የሙያ ብቃት ማረጋገጥ ደረጃ 4 የብቃት ማረጋገጫ ዘርፍ አንዱ ሲሆን ይህንን ስራ ተግባራዊ ለማድረግ ሚያስችል የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ድጋፉ ስራውን በቀጣይነት ለማሰራት የሚያስችል አቅም ይፈጥራል ተብሎ ይታሰባል:: |
- Hits: 966
የህዝብን ጥቅም ያስቀደመ ፍትሃዊ የነዳጅ አቅርቦት፣ስርጭትና ግብይት እንዲሰፍን ትኩረት ሰጥተን እንሠራለን፡፡
የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት በቢሾፍቱ ከተማ ከነዳጅ አከፋፋይ ኩባኒያዎች ጋር የነዳጅ ገበያ ድርሻ ውሳኔን በተመለከተ በተደረገ ውይይት ላይ “ከፍተኛ የሀገር ሀብት ፈሶበት ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባ ነዳጅ የህዝብን ጥቅም ባስቀደመ ፍትሃዊ፣ሕግን ያከበረ የአቅርቦት፣ስርጭትና የግብይት ስርዓት እንዲኖር ለማድረግ ሚንስቴር መ/ቤቱ በዘርፉ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ጥብቅ ክትትል ያደርግበታል” በማለት አጽእኖት ሰጥተው ገልፀዋል፡፡
ከነዳጅ ስርጭትና ግብይት ጋር ተያይዞ ከፍተኛ ሕገ-ወጥነት እንደሚስተዋል የተናገሩት ሚኒስትሩ ይህን ተከትሎ ማደያዎችን በማድረቅ የነዳጅ አቅርቦት ችግር እንዳለ ለማስመሰል በሚደረገው ጥረት ላይ ጠበቅ ያለ እርምጃ መውሰድ የሚያስችል የአሰራር ስርዓት እየተዘረጋ መሆኑን አመላክተው ሕገወጥነቱ በሚፈጥራቸው ሰውሰራሽ እጥረቶች በሚፈጥረው ተፅዕኖ ምክንያት ከሌለ ሀብት ላይ ከፍተኛ በጀት ተመድቦ ነዳጅ የመጨመር ፍላጎት እንደማይኖር ተናግረዋል፡፡ የገበያ ድርሻ ድልድሉንም በተመለከተ በየሶስት ወሩ ወቅታዊ ሁኔታዎችን ባገናዘበ መልኩ የሚከለስ ሲሆን የሁሉንም ሀሳብ በእኩልነት ተመልክተን ፍትሃዊ ክፍፍል እንዲኖር እናደርጋለን ብለዋል፡፡
|
- Hits: 972
የነዳጅ ግብይት ረቂቅ አዋጅ መፅደቅ በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ፡፡
የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ክህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ንግድና ቱሪዝም ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጋር በነዳጅ ግብይት ረቂቅ አዋጅ ላይ በዛሬው ዕለት ባደረጉት ውይይት፤ የረቂቅ አዋጁ መፅደቅ በነዳጅ ግብይት ላይ የሚስተዋሉ ሕገ-ወጥ ተግባራትን ለመቆጣጠር ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የቋሚ ኮሚቴው አባላት በውይይቱ ላይ በነበራቸው ቆይታ፤ በአዋጁ አስፈላጊነት እና ቀደም ሲል ይሰራበት የነበረው የነዳጅና የነዳጅ ውጤቶች አቅርቦት ሥራን ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ 838/2006 መተካት ያስፈለገበት ዋናኛ ምክንያት እና በአዋጁ ይዘት ላይ ማብራሪያ የጠየቁ ሲሆን በረቂቅ አዋጁ ይዘት ላይም አስተያየት ሰጥተዋል፡፡
ባለስልጣን መ/ቤቱ ከአባላቱ በቀረቡለት ጥያቄዎች ላይ ሰፊ ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን በዋነኝነት ረቂቅ አዋጁን ማዘጋጀት ያስፈለገበት ምክንያት ቀደም ሲል በነበረው አዋጅ ያልተካተቱ ወሳኝ ጉዳዮች መኖራቸው፣ የቀደመው አዋጅ አቅርቦት ላይ ትኩረት የሚያደርግና ስርጭትን ግብይትን የተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ክፍተት ያለው መሆኑ፣ የቁጥጥር ስራውን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ የተደረጉ የአሰራር ስልቶችን ያማያካትትና ወቅታዊ ባለመሆኑ እና በተለይ በግብይት ላይ የሚስተዋሉ ሕገ-ወጥነት ላይ ጠበቅ ያለ እርምጃ መውሰድ ያማያስችል በመሆኑ ነው የሚል ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡
በውይይቱ ማጠቃለያ የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ክብርት ወ/ሮ አሻ ያህያ የአዋጁ ወቅታዊነት እና አስፈላጊነት በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት ያማያጠያይቅ ጉዳይ መሆኑን ገልፀው ቋሚ ኮሚቴው ከባለስልጣን መ/ቤቱ ከተሰጠው ማብራሪያ በተጨማሪ በቀጣይ በትኩረት የሚመለከተው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
|
- Hits: 1098
ከነዳጅ አከፋፋይ ኩባኒያዎች ጋር በነዳጅ ግብይት ሂደቱ በሚስተዋሉ ችግሮች ዙሪያ ውይይት ተካሄደ ፡፡
የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ጋር በጋራ በመሆን በነዳጅ ስርጭትና ግብይት ላይ በሚስተዋሉ ችግሮች ዙሪያ ያዘጋጀው የምክክር መድረክ ሁሉም የነዳጅ አከፋፋይ ኩባኒያዎች በተገኙበት በቢሾፍቱ ከተማ ተካሂዷል፡፡
የምክክር መድረኩ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚንስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)፣ የሀገር ውስጥ ንግድ ላይሰንሲንግ ዘረፍ ሚኒስትር ዲኤታ አብዱልሃኪም ሙሉ (ዶ/ር)፣የነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ዋና ስራ አስፈፃሚ እስመለዓለም ምህረቱ እና የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሠሀርላ አብዱላሂ በተገኙበት ተካሂዷል፡፡ በውይይቱ ላይ የሀገር ውስጥ ንግድን ሕጋዊነት ለማስጠበቅና የተረጋጋ የንግድ ስርዓት እንዲኖር ለማስቻል በተለያዩ ዘርፎች በተሰሩ ስራዎች የተገኘን ውጤት በነዳጅ ግብይት ሂደት ላይ ለማምጣት ትኩረት አድርጎ መስራት የሚኒስቴር መ/ቤቱ አቋም እንደሆነ በሚኒስቴር መ/ቤቱ በኩል ተገልጿል፡፡
በነዳጅ አቅራቢ ድርጅት በኩል እንደተነገረው በነዳጅ አቅርቦት ላይ እንደ ሀገር የሚገለጽ እጥረት አለመኖሩ፣ ሀገሪቱ በዓመት አራት ቢሊየን ዶላር መድባ ነዳጅ እንደምታስገባ ሆኖም በጅቡቲ ሆራይዘን የጭነት አቅም እንደ ችግር የሚገለፅ መሆኑ የተጠቆመ ሲሆን ለችግሩ መባባስ ግን በዋነኝነት በነዳጅ ስርጭት ላይ በየደረጃው የሚስተዋሉ የስነምግባር ጥሰቶች ተጠቃሽ መሆናቸው ተመላክቷል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ከተለያዩ ክልል ነዋሪዎች በተሰጠ መረጃ መሠረት የነዳጅ አቅርቦት ችግር ሳይኖር ማደያዎች ላይ የደረሰ ነዳጅ ምሽትን ተገን አድርጎ በሕገወጥ መንገድ እንደሚወጣ ደርሰንበታል በማለት የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ ተናግረዋል፡፡
በባለስልጣን መ/ቤቱ በኩል እንደተነገረው በአጠቃላይ በሀገሪቱ 560 ወረዳዎች ማደያ እንደሌላቸው የተነገረ ሲሆን ከዚህ በኋላ የሚገነቡ ነዳጅ ማደያዎች እነዚህን ቦታዎች ያማከለ ፣ በፀደቀው የነዳጅ ማደያወች ደረጃ መስፈርት መሠረት እንደሚሆን፣ የነዳጅ አቅርቦቱም ኢኮኖሚክ ዞን ተብለው በተለዩ 22 ከተሞች ላይ ትኩረት አድርጎ የሚቀርብ መሆኑን በዋና ዳይሬክተሯ ሰሀርላ አብዱላሂ ተነግሯል፡፡ በነዳጅ አከፋፋይ ኩባኒያዎች በኩል ከገበያ ድርሻ ፍትሃዊነት፣ የነዳጅ ማደያ ፈቃድ አሰጣጥ፣ በዘርፉ የሚስተዋሉ የስነምግባር ጥሰቶችና የቁጥጥር ሂደቱን በተመለከተ በተዘጋጁ የአሰራር ስርዓቶች አተገባባር ጋር በተያያዘ በርከት ያሉ ሃሳቦች ተሰንዝረው ውይይት ተደርገባቸዋል፡፡ በውይይቱ ማጠቃለያ በተሰጠ አቅጣጫ ኢንደስትሪው ስነምግባርና ሃላፊነትን ተላብሶ ጤናማ ውድድርን መሠረት አድርጎ ሊሠራ ይገባል የሚል አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡
|
- Hits: 949
More Articles ...
Page 2 of 6