የኢነርጂ መጠቀሚያ ዕቃዎች የጥራት እና የኢነርጂ ብቃት ደረጃ ላይ ስልጠና ተሰጠ፡፡

 

ጥር 23/2017 (ነ.ኢ.ባ)

አነስተኛ ኢነርጂ ብቃት ደረጃ (MEPS) ለወጣላቸው ከውጭ ሀገራት ለሚገቡ የኤሌክትሪክ መገልገያ ዕቃዎች የቅድመ ጭነት የጥራት ቁጥጥር ስርዓት (pre-export verification of conformity) የተመለከተ ስልጠና የቁጥጥር ስራውን ለሚሠሩ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ባለሙያወች ተሰጠ፡፡

በባለስልጣን መ/ቤቱ የተዘጋጀው ይህ ስልጠና ብሔራዊ ኢነርጅ ብቃትና ቁጠባ ስትራቴጂን ለማሳካት በተቀረጹ ፕሮግራሞች አንዱ በሆነው የኤሌክትሪክ መገልገያ ዕቃዎች ኢነርጂ ብቃት ማሻሻያ ዓላማን ተፈፃሚ ለማድረግ ኢነርጂ አባካኝ ተብለው በተለዩ ከውጭ ሀገራት የሚገቡ የኤሌክትሪክ ሞተር፣ ማቀዝቃዣ ማሺኖች፣ጄኔሬተሮች፤ማከፋፈያዎችና ሶኬቶች ወደ ሀገር ውስጥ ከመግባታቸው አስቀድሞ ቁጥጥር ለማድረግ የሚያስችል የምርቶች ዝቅተኛ ኢነርጂ ብቃት ደረጃ የተመለከተ ግንዛቤ ለመፍጠር እንደሆነ ተነግሯል፡፡

የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይርክተረ አቶ ዲባራ ፉፋ ስልጠናውን በተመለከተ ባስተላለፉት መልዕክት፤ በአገራችን የሀይል አጠቃቀም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን ጠቁመው ለኢነርጂ ክፍለ -ኢኮኖሚ የሚሆን በቂ የኢነርጂ ፍጆታና ፍታሀዊ ተጠቃሚነት እንዲኖር ለማድረግ መንግስት የኢነርጂ አጠቃቀም ቁጥጥር እና ድጋፍ በመዘርጋት ለሁሉም በሁሉም ኢነርጂ ተጠቃሚ ዘርፎች በተለይም ለኢንዱስትሪዎች ሚፈልጉትን የሀይል መጠን ለማዳረስ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በንግድና ቀጣናዊ ትስር ሚኒስቴር የሕግ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ይርሳው ዘውዴ የስልጠናውን አስፈላጊነት አስመልክቶ እንደገለጹት በሀገር ውሰጥ የሚመረቱ፤ወደ ሀገር ውሰጥ የሚገቡ እና ወደ ውጪ ሀገር የሚላኩ የኢትዮጵያ ደረጃ የውጣላቸው ምርቶች ፤አገልግሎቶች እና ሂደቶች የጥራት ደረጃቸውን የጠበቁ መሆናቸውን በመቆጣጠር በሰዎች ፤በእሰሳት እና በአካባቢ ጤና እንዲሁም በሀገር ጥቅም ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንያስከትል የኢትዮጵያ ደረጃዎች አዘገጃጅትና ማስተገበሪያ ሥርዓት ለመደንገግ በወጣው መሠረት አዋጅ ቁጥር 1343 /2016 አዋጁ ላይ እንደተደነገገ አስረድተው ይህንን ለማስፈፀም የቁጥጥር ስራዎች እየተሠሩ ነው ብለዋል፡፡
 
  • Hits: 1478

Contact Us

Petroleum and Energy Authority 

P.O.BOX 2554

Tel +251 

FAX +251

Email pea.info@pea.gov.et

Addis Ababa

Ethiopia

Address

Addis Ababa Kadco Group building #2 From 7th to 8th floor. Ethio china Friendship Avenue around Wello sefere.