ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አመራሮች ጋር ውይይት ተካሄደ
ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አመራሮች ጋር ውይይት ተካሄደ
**********************************************************************************************************
የካቲት 24/2017 (ነ.ኢ.ባ)
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እና በነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ከፍተኛ ኃላፊዎች መካከል በቀጣይ የተቋማቱ ግንኙነትና ስራዎች ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ፡፡
የተቋማቱ የበላይ ኃላፊዎች የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢ/ር ጌቱ ገረመው እና የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሠሀርላ አብዱላሂ በተገኙበት የተደረገው ውይይት በዋነኝነት አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በስራ ላይ ሰለማዋል፣ የኤሌክትሪክ ኃይልን በብቃትና ቁጠባ ስለመጠቀም፣ የኃይል ብክነትን መቀነስ፣ የኃይል መቋረጥን ሙሉ በሙሉ ማስቀረት ስለሚቻልበት ሁኔታ፣አስተማማኝ የኃይል አቅርቦትን ስለማረጋገጥ እና የኤሌክትሪክ አቅርቦትና አገልግሎት አሰጣጥ የተቀመጠለትን ስታንዳርድ ማሟላትን የተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሂዷል፡፡
በቀጣይ የኃይል አቅርቦት አስተማማኝነት፣ጥራትና ደህንነትን ለማስጠበቅ በሚሰሩ ስራዎች ዙሪያ ከተለያዩ አካላት በሚውጣጡ የባለሙያዎች ኮሚቴ የሚቋቋም መሆኑ ተነግሯል፡፡
|
- Hits: 2629