የህዝብን ጥቅም ያስቀደመ ፍትሃዊ የነዳጅ አቅርቦት፣ስርጭትና ግብይት እንዲሰፍን ትኩረት ሰጥተን እንሠራለን፡፡
የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት በቢሾፍቱ ከተማ ከነዳጅ አከፋፋይ ኩባኒያዎች ጋር የነዳጅ ገበያ ድርሻ ውሳኔን በተመለከተ በተደረገ ውይይት ላይ “ከፍተኛ የሀገር ሀብት ፈሶበት ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባ ነዳጅ የህዝብን ጥቅም ባስቀደመ ፍትሃዊ፣ሕግን ያከበረ የአቅርቦት፣ስርጭትና የግብይት ስርዓት እንዲኖር ለማድረግ ሚንስቴር መ/ቤቱ በዘርፉ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ጥብቅ ክትትል ያደርግበታል” በማለት አጽእኖት ሰጥተው ገልፀዋል፡፡
ከነዳጅ ስርጭትና ግብይት ጋር ተያይዞ ከፍተኛ ሕገ-ወጥነት እንደሚስተዋል የተናገሩት ሚኒስትሩ ይህን ተከትሎ ማደያዎችን በማድረቅ የነዳጅ አቅርቦት ችግር እንዳለ ለማስመሰል በሚደረገው ጥረት ላይ ጠበቅ ያለ እርምጃ መውሰድ የሚያስችል የአሰራር ስርዓት እየተዘረጋ መሆኑን አመላክተው ሕገወጥነቱ በሚፈጥራቸው ሰውሰራሽ እጥረቶች በሚፈጥረው ተፅዕኖ ምክንያት ከሌለ ሀብት ላይ ከፍተኛ በጀት ተመድቦ ነዳጅ የመጨመር ፍላጎት እንደማይኖር ተናግረዋል፡፡ የገበያ ድርሻ ድልድሉንም በተመለከተ በየሶስት ወሩ ወቅታዊ ሁኔታዎችን ባገናዘበ መልኩ የሚከለስ ሲሆን የሁሉንም ሀሳብ በእኩልነት ተመልክተን ፍትሃዊ ክፍፍል እንዲኖር እናደርጋለን ብለዋል፡፡
|
- Hits: 972