የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪ ኃይል መሙሊያ ጣቢያ መሠረተ ልማት ግንባታ ረቂቅ መመሪያ ላይ ውይይት ተደረገ፡፡

 

የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪ ኃይል መሙሊያ ጣቢያ መሠረተ ልማት ግንባታ የተመለከተ ረቂቅ መመሪያ ላይ ከነዳጅ አከፋፋይ ኩባኒያዎች ጋር ውይይት ተደረገ፡፡

በነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን የተዘጋጀው ረቂቅ መመሪያ በዋነኝነት ኃይል መሙሊያ ጣቢያ መሠረተ ልማት ግንባታ ከደህንነት ጋር በተያያዘ ሊኖር የሚገባው ቴክኒካል ስታንዳርድ፣ ፈቃድ አሰጣጥ መስፈርት እና ታሪፍን የተመለከቱ ጉዳዮችን የተካተተበት ነው፡፡

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሠሀረላ አብዱላሂ በውይይቱ ላይ በሰጡት ማብራሪያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ በስፋት እየገቡ ከመሆናቸው ጋር በተያያዘ ለህዝብ አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ የሃይል መሙሊያ ጣቢያዎች መኖር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ባለስልጣን መ/ቤቱ በሕግ ከተሰጡት ኃላፊነቶች መነሻነት በዘርፉ የሚኖር የሃይል አቅርቦት ጥራት ፣ አስተማማኝነት እና ደህንነቱ የተጠበቀ አገልግሎት አሰጣጥን ለመቆጣጠር ሲባል መመሪያውን ማዘጋጀት ማስፈለጉን ገልፀዋል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ አቶ አህመድ ሰኢድ የኢነርጂ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር በመመሪያ ዝግጅት ሂደት ላይ ከነዳጅ አከፋፋይ ኩባንያዎች ጋር በተናጠል መወያየት ያስፈለገው የሃይል መሙሊያ መሠረተ ልማት ግንባታን በተመለከተ ከሌሎች ሀገራት ተሞክሮ በመነሳት መሠረተ ልማት ለመገንባት ተጨማሪ ቦታ ሳያስፈልግ በነዳጅ ማደያዎች የኤሌክትሪክ ተሸርካሪዎችን ሃይል መሙላት የሚያስችል ስራን ጎን ለጎን መስራት የሚቻልበትን ዕድል ለመፍጠር መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በቀረበው ረቂቅ መመሪያ መነሻነት በተደረገ ውይይት ከተሳታፊዎች የተለያዩ አስተያየቶች በግብዓትነት የተሰጡ ሲሆን ከነዚህ መካከል በዋነኝነት በዘርፉ መሳተፍ ለሚፈልጉ አካላት የሚሰጥ ማበረታቻ፣ የሃይል አቅርቦት ጥራትና አስተማማኝነት እና ዘርፉ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ሁሉንም ያካተተ ተጨማሪ ውይይት ተደርጎ መዳበር አለበት ሲሉ ሃሳባቸውን ሠንዝረዋል፡፡

በማጠቃለያው ላይ እንደተገለፀው በቀጣይ ሁሉን አካታች የሆነ ውይይት ከተለያዩ ዘርፎች ከተውጣጡ አካላት ጋር እንደሚደረግና መመሪያው ፀድቆ ወደስራ የሚገባበትን ሂደት ለማፋጠን እንደሚሠራ ተነግሯል፡፡

 
  • Hits: 1060

Contact Us

Petroleum and Energy Authority 

P.O.BOX 2554

Tel +251 

FAX +251

Email pea.info@pea.gov.et

Addis Ababa

Ethiopia

Address

Addis Ababa Kadco Group building #2 From 7th to 8th floor. Ethio china Friendship Avenue around Wello sefere.