የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ቀጠና ሀገራት ኢነርጂ ተቆጣጣሪ አካላት ማህበር(RAERESA) ስብሰባውን በአዲስ አበባ በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
በምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ሀገራት የጋራ ገበያ (ኮሜሳ) ስር የሚገኘው የቀጠናው ሀገራት ኢነርጂ ተቆጣጣሪ አካላት ማህበር RAERESA የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት ትስስርና ንግድ የሚመራበት የሕግ ማዕቀፍና ወጥነት ያለው የኤሌክትሪክ ታሪፍ ቁጥጥር ላይ ያተኮረ አውደ ጥናት ከመስከረም 8-10 ባሉት ሶስት ተከታታይ ቀናት በአዲስ አበባ በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
በኮሜሳ የቀጠናው ሀገራት ኢነርጂ ተቆጣጣሪ ማህበር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሞሀሙዲኒ ኢሰኢፍ በአውደ ጥናቱ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር ኮሜሳ በአባል ሀገራቱ መካከል የኢኮኖሚ ውህደት እንዲፈጠር እየሠራ ይገኛል ብለዋል፡፡
የኢኮኖሚ ውህደቱ አንድ አካል የሆነው በአባል ሀገራቱ መካከል የሚደረገው የኤሌክትሪክ ሃይል ንግድ የሚመራበትን ማዕቀፍ ለማዘጋጀት የተጀመረው ፕሮጀክት በቀጠናው ሀገራት መካከል የሚገኘውን የሃይል አቅርቦት ትስስር ይበልጥ እንደሚያሳድገው ተናግረዋል፡፡
ሞሀሙዲኒ እንደገለፁትም ፕሮጀክቱን ለመተግበር በአፍሪካ ልማት ባንክ እና በኮሜሳ ትብብር 1 ነጥብ 5 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር የተመደበ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን የፈቃድና ቴክኒካል ሬሌሽን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ባህሩ ኦልጂራ በአወደ ጥናቱ መክፈቻ ስነ-ስትዓት ላይ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ በቀጠናው ለሚገኙ ሀገራት ለኬኒያ፣ ሱዳንና ጂቡቲ የኤሌክትሪክ ሃይል በማቅረብ ላይ እንደምትገኝ ገልፀው በቀጣይም ለሌሎች የቀጠናው ሀገራት የሀይል አቅርቦት ትስስሩን ለማጠናከር በሂደት ላይ ትገኛለች ብለዋል፡፡
አቶ ባህሩ ጨምረውም እንደገለፁት ኢትዮጵያ ባላት ሰፊ የታዳሽ ኢነርጂ አቅም የምስራቅ አፍሪካ የታዳሽ ኢነርጂ ማዕከል ለመሆን እየሠራች ትገኛለች ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ውይይቱ የመጀመሪያው ቀን በዋነኝነት የኤሌክትሪክ ታሪፍ ወጥነት ኖሮት መቆጣጠር የሚያስችል ሞዴል ቀርቦ ጥናቱን ባጠናው አማካሪ ድርጅት ገለፃ ተደርጓል፡፡
የተሳታፊ ሀገራቱ ተወካዮችም ሞዴሉን በሀገራቱ ካለው ነባራዊ ሁኔታ ጋር ማጣጣም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡ ዐውደ ጥናቱ ባለፉት ሶስት ቀናት ሲካሄድ ቆይቶ በዛሬው ዕለት የሚጠናቀቅ ሲሆን በማህበሩ አባል ሀገራት ፕሮጀክቱን ለማስፈፀም የሚያስችሉ የተለያዩ ውሳኔዎች ይተላለፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
|
- Hits: 445
19ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀንን ምክንያት በማድረግ ውይይት ተደረገ
የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በብሔራዊ ደረጃ ለ19ኛ ጊዜ ለማክበር በዝግጅት ላይ የሚገኝ ሲሆን ቀኑን በማስመልከት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተዘጋጀ የጥናት ፁሁፍ ላይ የባለስልጣን መ/ቤቱ ሠራተኞች ህዳር 19/2017 ተወያይተዋል፡፡
|
- Hits: 631
ኢነርጂ አስተዳደር ስርዓት ደረጃ (Energy Management System Standard) ስልጠና በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡
ኢነርጂ አስተዳደር ስርዓት ደረጃ (Energy Management System Standard) በተመለከተ ለከፍተኛ ኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ኢንዱስትሪ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ለተከታታይ አምስት ቀናት የሚሰጠው ስልጠና በዛሬው ዕለት በአዳማ ከተማ በይፋ ተጀምሯል፡፡
የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን የኢነርጂ ብቃት ማረጋገጥና ቁጠባ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ዘውገ ወርቁ በስልጠና መርሀግብሩ ማስጀመሪያ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የኢነርጂ ማኔጅመንት ሲስተም ስታንዳርድ የኃይል አጠቃቀምን በማሻሻል የተሻለ ትርፍና ዘለቄታዊ የኃይል ደህንነት እንዲኖር እንዲሁም ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ጠቅሰዋል።
ስልጠናው የሚኖረው ፋይዳን በተመለከተ የኢነርጂ ማኔጅመንት ሲስተም ስታንዳርድ በመጠቀም የኃይል ብክነትን በማስቀረት የኤሌክትሪክ ፍጆታ ክፍያን መቀነስና ተወዳዳሪ ኢኮኖሚ ለመፍጠር፤ እንዲሁም የካርበን ዳይ ኦካሳይድ ልቀትን በመቀነስ አካበቢያዊ ብክለትን ለመከላከል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ገለጸዋል።
የኢነርጂ ማኔጅመንት ሲስተም ስታንዳርድ አተገባበርን በተመለከተ በአገሪቱ ውስጥ ያሉ ከፍተኛ ሃይል ተጠቃሚ ኢንዱስትሪዎች ላይ ኢነርጂ ኦዲትን ተግባራዊ በማድረግ ፍጆታቸውን ማወቅ እና ያለአግባብ የሚባክን ኢነርጂን በብቃትና ቁጠባ ላይ የተመሠረተ አጠቃቀም እንዲኖር በማስቻል የኢነርጂ ፍጆታን ማሻሻል ይቻላል ብለዋል ፡፡
የኢነርጂ ኦዲት መረጃን መሠረት በማድረግ በቂ ክትትል፤ ድጋፍና የኢነርጂ አጠቃቀም ትንታኔና በቴኒካል ድጋፍ ክፍተት ዙሪያ ያሉትን ችግሮች ለማሻሸል ከሚኖረው ከፍኛ አስተዋእፆ በተጨማሪ ዋጋን መሠረት በማድረግ የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ትንታኔ የመስጠት ሂደትን የሚያካትት ነው በማለት አብራርተዋል፡፡
በመጨረሻም ከፍተኛ ኃይል ተጠቃሚ ኢንዱስትሪዎች የኢነርጂ ማኔጅመንት ሲስተም ስታንዳርድን ተግባራዊ በማድረግ የኢነርጂ አጠቃቀም ብቃትና ቁጠባ እንደ ቁልፍ ስራ በመተግበር በተለይም የኢነርጂ ኦዲት አገልግሎትን በመጠቀም ሁሉም ሰልጣኞች የወሰዱትን ስልጠና ተግባራዊ በማድረግ የኢነርጂ ልማት ክፍለ-ኢኮኖሚው ላይ ትልቅ እምርታዊ ለውጥ ማምጣት እንደያስሚያስችል አስገንዝበዋል፡፡
|
- Hits: 785
ሂዩማን ኢነርጂ አነስተኛ ግሪድ ፕሮጀክት በፕላኑ መሠረት እየተተገበረ መሆኑ ተገለፀ።
የኤሌክትሪክ ሃይል አልሚ ድርጅት በሆነው ሂዩማን ኢነርጂ ሃላፊነቱ የተውሰነ የግል ድርጅት በመልማት ላይ የሚገኘው 254 ኪሎ ዋት ሶላር ሚኒ ግሪድ ፕሮጀክት ሂደት በባለስልጣን መ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሠሀረላ አብዱላሂ እና የቴክኒክ ብድን ሃላፊ በሆኑት አቶ ባህሩ ኦልጅራ ተጎበኘ። ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሠሀረላ አብዱላሂ ከመስክ ምልከታው በኋላ እንደገለፁት ሂዩማን ኢነርጂ ከባለስልጣን መ/ቤቱ አስፈላጊውን መስፈርት አሟልቶ የኢንቨስትመንት፣የማመንጨት እና የኦፕሬሽን ፈቃድ ወስዶ በአጭር ጊዜ ውስጥ ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅ እና አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ደረጃ ላይ የሚገኝ መሆኑ አንዳስደሰታቸው ገልፀው በዘርፉ ለሚደረግ ኢንቭስትምንት ምሳሌ የሚሆን አፈፃፀም መመልከታቸውን ገልፀዋል። በተጨማሪም በቀጣይ ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅ የሚያስችል አስፈላጊ ድጋፍ በባለስልጣን መ/ቤቱ በኩል እንደሚደረግ አስታውቀዋል። ሂዩማን ኢነርጂ ኢትዮጵያ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት ከአንድ አመት በፊት ከባለስልጣን መ/ቤቱ ፈቃድ በመውሰድ በሱማሌ ክልል ፈፋን ዞን በሸደር የስደተኞች ካንፕ ተጠልለው ለሚገኙ ሆስት ኮሚኒቲ የኤሌክትሪክ ሃይል አገልግሎት ማቅረብ የሚያስችል ሀይል የማመንጨት ሥራ ተጠናቆ ኤሌክትሪክ ማስተላለፊያና ማከፋፈያ መሠረተ ልማት ዝርጋታ ዝግጅት ላይ የሚገኝ ሲሆን በቅርቡ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ደረጃ ላይ እንደሚገኘ በምልከታው ለመረዳት መቻሉ ተነግሯል። የባለስልጣን መ/ቤቱ ቴክኒካል ሬጉሌሽን ዳይሬክተር አቶ ባህሩ ኦልጂራ እንደገለፁት ፕሮጀክቱ በተቀመጡ የፈቃድ ግዴታዎች መሰረት ቴክኒካል መሥፈርቶችን አሟልቶ በፕሮጀክት ፕላን መሠረት እየተካሄደ መሆኑን መመልከታቸውን ገልጸዋል። ከዚህ ጋር በተያያዘ መረጃ ሀገራችን ከታዳሽ ሀይል ኤሌክትሪክ ማመንጨት የሚያስችል ትልቅ አቅም ያላት ሲሆን ብሔራዊ ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም ከግሪድ ርቀው ለሚገኝ የሀገሪቱ ክፍሎች 35 በመቶ ያህሉ በአነስተኛ ግሪድ ሀይል ማመንጫ የሚሽፈን ሲሆን ለዚህ አላማ ስኬት ባለስልጣን መ/ቤቱ በዘርፉ ለሚደረግ ኢንቨስትመንት የህግ ማዕቀፍ በማዘጋጀትና አስፈላጊ መረጃዎችን ለአልሚዎች በመስጠት የግሉን ኢንቨስትመንት በማበረታታት ላይ እንደሚገኝ በጉብኝቱ ማጠቃለያ ላይ ተገልጿል። |
- Hits: 1130
More Articles ...
Page 1 of 6