ከከፍተኛ ኤሌክትሪክ ሃይል ተጠቃሚ ፋብሪካዎች ጋር ኢነርጂ አስተዳደር ፈቃደኝነት ስምምነት ተፈረመ።

 

ር 24/2017 (ነ.ኢ.ባ)

ከሶስት ከፍተኛ ኤሌክትሪክ ሃይል ተጠቃሚ ፋብሪካዎች፤ ድሬደዋ ምግብ ኮምፕሌክስ፣ ቱሬ ሲሚንቶ ፋብሪካ እና ሂይኒከን ኢትዮጵያ ስር ከሚገኘው ሀረር ቢራ ፋብሪካ ጋር የፈቃደኝነት ኢነርጂ አስተዳደር ስምምነት (Voluntary energy management agreement) ባለስልጣን መ/ቤቱ ተፈራረመ፡፡

በባለስልጣን መ/ቤቱና በፋብሪካዎቹ መካከል የተፈፀመው ስምምነት ፋብሪካዎቹ በምርት ሂደት የሚጠቀሙትን ኢነርጂ ምርትን ሣይቀንሱ በተለያዩ ምክንያቶች የሚያጋጥም የኤሌክትሪክ ሃይል ብክነትን ለመቀነስ የሚያስችላቸውን እርምጃዎች ለማከናወን ሲሆን በባለስልጣን መ/ቤቱ በኩል ይህን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችላቸውን ድጋፍና ክትትል ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት ነው፡፡

ከስምምነቱ ሠነድ ለመረዳት እንደተሞከረው የስምምነት ሂደቱ የሚጀምረው ፋብሪካዎቹ እየተጠቀሙ ያሉትን ኢነርጂ ኦዲት በማስደረግ የሚባክን ኢነርጂ መጠንን በማወቅ በሂደት የማሻሻያ ሥራዎችን ለመስራትና ብክነቱን ለመቀነስ ዕቅድ አስቀምጠው የሚተገብሩት ሲሆን ባለስልጣን መ/ቤቱ የዕቅዱን ሂደት በመከታተል እና የሚያስፈልጉ ድጋፎችን በመስጠት ውሉ የሚፈፀም ይሆናል፡፡

ባለስለጣኑን ወክለው ስምምነቱን የፈረሙት የኢነርጂ ብቃትና ቁጠባ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዘውገ ወርቁ እንደገለጹት በከፍተኛ ሃይል ተጠቃሚ ኢንደስትሪዎች ላይ የሚባክን ኢነርጂን መቀነስ እንደ ሀገር የሚባክን ኢነርጂን ለመቀነስ እንደሚያስችል፣በኤሌክትሪክ መስመሮች ላይ የሚያጋጥም መጫናነቅና የሃይል መቆራረጥን እንደሚቀነስ ብሎም አለአግባብ የሚጨምር የኢነርጅ ፍላጎትን በመቀነስ ኤሌክትሪክ ሃይል ለሚፈለግባቸው አከባቢዎች ማድርስ እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡

ጨምረውም እንደገለጹት ኢንደስትሪዎች የሚጠቀሙትን ኢነርጂ ከብክነት በመከላከል የኤሌክትሪክ ክፍያቸውን መቀነስ እንደሚያስችላቸውና በኢነደስትሪ ውስጥ ዘላቂና ተወዳዳሪ ሆነው እንዲቀጥሉ የሚያስችል አቅም እንደሚፈጥር ገልፀዋል፡፡ በቀጣይም ከሌሎች ኢንደስትሪዎች ጋር ስምምነቱ እንደሚፈፀም እና ስምምነቱን ከፈረሙት ጋር ደግሞ የክትትልና ድጋፍ ሥራ የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል፡፡

ባለስልጣን መ/ቤቱ ባስለፍነው ሳምንት ስምምነቱን ከተፈራራመቸው ሶስት ፋብሪካዎች በተጨማሪ ከዚህ ቀደም ስምምነት ካደረገው ናሽናል ሲሚንቶ ሼር ካንፓኒ ስምምነቱን ተከትሎ የተተገበሩ ስራዎች ላይ ክትትልና በቀጣይ ሊደረጉ በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡
 

 

  • Hits: 2164

Contact Us

Petroleum and Energy Authority 

P.O.BOX 2554

Tel +251 

FAX +251

Email pea.info@pea.gov.et

Addis Ababa

Ethiopia

Address

Addis Ababa Kadco Group building #2 From 7th to 8th floor. Ethio china Friendship Avenue around Wello sefere.