ብሔራዊ የነዳጅ ሪፎርም እስቲሪንግ ኮሚቴ ባለፉት አስር ወራት የነበረውን የነዳጅ ሪፎርም አፈጻጸም በመገምገም የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

 

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚንስቴር በማህበራዊ ትስስር ገፁ እንዳስታወቀው ብሔራዊ የነዳጅ ሪፎርም እስትሪንግ ኮሚቴ ሚያዚያ 30/2016 ዓ.ም በንግድና ቀጣናዊ ትስሰር ሚኒስትሩ አቶ ገብረመስቀል ጫላ ሰብሳቢነትና በዶ/ር ዓለሙ ስሜ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ሚኒስትር ም/ሰብሳብነት ፣ የገንዘብ ሚኒስቴር ፣የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን፣ የኢት/የነዳጅ አቅራቢ ድርጅት እና ኢትዮ ቴሌኮም በአባልነት በተገኙበት በተደረገ የኮሚቴው ስብሰባ ሪፎርሙ ተገምግሞ የተለያዩ ውሳኔዎች ተላልፈዋል፡፡

ባለፉት አስር ወራት በታቀደው መሰረት ስራዎች መሰራታቸውን የተመለከተው ኮሚቴው በዲጂታል የነዳጅ ግብይት የሚካሄደውን መረጃ በማዕከል ለማደራጀት እየተጠና ያለው ሲስተም ልማት መጠናቀቅ ደረጃ ላይ መድረሱን፣ ነዳጅ ስርጭትን ከግዥ ትዕዛዝ ጀምሮ ከወደብ ከጫነ በኋላ ማደያ እስኪራገፍ ድረስ ያለውና ከተራገፈ በኋላ የነዳጅ ስርጭቱ በድጅታል መፈፀሙን ኦዲት ለማድረግ የሚያስችል ሲስተም ጥናት ተጠናቆ ወደ ሙከራ ትግበራ መግባት መቻሉና እስካሁን የታለመለት የነዳጅ ድጎማን ያለአግባብ የወሰዱ ተሽከርካሪዎች ላይ ኦዲት በማድረግ እርምጃ መውሰድ መጀመሩ በጠንካራ አፈጻጸም ገምግሟል።

እንዲሁም አሁን ያለው የነዳጅ ሪፎርም ተጠናክረው መቀጠሉ በነዳጅ ዋጋ ማረጋጊያ ፈንድ ላይ የነበረውን ከፍተኝ የዕዳ ጫና ወደ 89 ቢሊየን ዝቅ ማድረጉ በጥንካሬ የተገመገመ ሲሆን ያልተጠናቀቁ ስራዎችም በፍጥነት እንዲጠናቀቁ ሲል ኮሚቴው አሳስቧል።

አዳዲስ የነዳጅ ኩባንያ እና የነዳጅ ማደያ መገንባት እንዲቆም ቀደም ሲል በተወሰነው ውሳኔ መሰረት አፈጻጸሙ ክትትል እንዲደረግበት፣ የተሽከርካሪ ሰሌዳ ምዝገባ አዲስ በሚለማው የተሽከርካሪ መረጃ ማዕከል እንዲደራጅ ሲል ኮሚቴው ውሳኔውን አስተላልፎል።

 

 
 

 

 
  • Hits: 1154

Contact Us

Petroleum and Energy Authority 

P.O.BOX 2554

Tel +251 

FAX +251

Email pea.info@pea.gov.et

Addis Ababa

Ethiopia

Address

Addis Ababa Kadco Group building #2 From 7th to 8th floor. Ethio china Friendship Avenue around Wello sefere.