በነዳጅና ኢነርጂ ዘርፍ ተቋማት ላበረከቱት አስተዋዕፆ ዕውቅና ተሰጠ፡፡
“የኢትዮጵያን ይግዙ!” የንግድ ሳምንትን ምክንያት በማድረግ በተካሄደ የዕውቅናና ሽልማት ስነ-ስርዓት ላይ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) እና ሚኒስትር ዲኤታዎች በተገኙበት በነዳጅና ኢነርጂ ዘርፍ ጉልህ አስተዋዕፆ ላበረከቱ ድርጅቶችና ሠራተኞች ዕውቅና ተሰጥቷል፡፡
በነዳጅ ዘርፍ በዲጂታል ነዳጅ ግብይት ከፍተኛ ሽያጭ ያከናወኑ የነዳጅ ኩባኒያዎች እና ማደያዎች ዕውቅና የተሰጣቸው ሲሆን በተለያዩ የኢነርጂ ሥራ ዘርፎች የላቁ ሥራዎችን ላበረከቱ ድርጅቶችም ዕውቅና ተሰጥቷል፡፡ በመጨረሻም የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን በመንግስት የተሰጠውን ተልዕኮ በመወጣት ሂደት የተሠጣቸውን ኃላፊነት በከፍተኛ ትጋት ለተወጡ ሠራተኞች ሽልማት ተሰጥቷል፡፡
|