ሂዩማን ኢነርጂ አነስተኛ ግሪድ ፕሮጀክት በፕላኑ መሠረት እየተተገበረ መሆኑ ተገለፀ።

 

የኤሌክትሪክ ሃይል አልሚ ድርጅት በሆነው ሂዩማን ኢነርጂ ሃላፊነቱ የተውሰነ የግል ድርጅት በመልማት ላይ የሚገኘው 254 ኪሎ ዋት ሶላር ሚኒ ግሪድ ፕሮጀክት ሂደት በባለስልጣን መ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሠሀረላ አብዱላሂ እና የቴክኒክ ብድን ሃላፊ በሆኑት አቶ ባህሩ ኦልጅራ ተጎበኘ።

ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሠሀረላ አብዱላሂ ከመስክ ምልከታው በኋላ እንደገለፁት ሂዩማን ኢነርጂ ከባለስልጣን መ/ቤቱ አስፈላጊውን መስፈርት አሟልቶ የኢንቨስትመንት፣የማመንጨት እና የኦፕሬሽን ፈቃድ ወስዶ በአጭር ጊዜ ውስጥ ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅ እና አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ደረጃ ላይ የሚገኝ መሆኑ አንዳስደሰታቸው ገልፀው በዘርፉ ለሚደረግ ኢንቭስትምንት ምሳሌ የሚሆን አፈፃፀም መመልከታቸውን ገልፀዋል። በተጨማሪም በቀጣይ ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅ የሚያስችል አስፈላጊ ድጋፍ በባለስልጣን መ/ቤቱ በኩል እንደሚደረግ አስታውቀዋል።

ሂዩማን ኢነርጂ ኢትዮጵያ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት ከአንድ አመት በፊት ከባለስልጣን መ/ቤቱ ፈቃድ በመውሰድ በሱማሌ ክልል ፈፋን ዞን በሸደር የስደተኞች ካንፕ ተጠልለው ለሚገኙ ሆስት ኮሚኒቲ የኤሌክትሪክ ሃይል አገልግሎት ማቅረብ የሚያስችል ሀይል የማመንጨት ሥራ ተጠናቆ ኤሌክትሪክ ማስተላለፊያና ማከፋፈያ መሠረተ ልማት ዝርጋታ ዝግጅት ላይ የሚገኝ ሲሆን በቅርቡ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ደረጃ ላይ እንደሚገኘ በምልከታው ለመረዳት መቻሉ ተነግሯል።

የባለስልጣን መ/ቤቱ ቴክኒካል ሬጉሌሽን ዳይሬክተር አቶ ባህሩ ኦልጂራ እንደገለፁት ፕሮጀክቱ በተቀመጡ የፈቃድ ግዴታዎች መሰረት ቴክኒካል መሥፈርቶችን አሟልቶ በፕሮጀክት ፕላን መሠረት እየተካሄደ መሆኑን መመልከታቸውን ገልጸዋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ መረጃ ሀገራችን ከታዳሽ ሀይል ኤሌክትሪክ ማመንጨት የሚያስችል ትልቅ አቅም ያላት ሲሆን ብሔራዊ ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም ከግሪድ ርቀው ለሚገኝ የሀገሪቱ ክፍሎች 35 በመቶ ያህሉ በአነስተኛ ግሪድ ሀይል ማመንጫ የሚሽፈን ሲሆን ለዚህ አላማ ስኬት ባለስልጣን መ/ቤቱ በዘርፉ ለሚደረግ ኢንቨስትመንት የህግ ማዕቀፍ በማዘጋጀትና አስፈላጊ መረጃዎችን ለአልሚዎች በመስጠት የግሉን ኢንቨስትመንት በማበረታታት ላይ እንደሚገኝ በጉብኝቱ ማጠቃለያ ላይ ተገልጿል።
 

Contact Us

Petroleum and Energy Authority 

P.O.BOX 2554

Tel +251 

FAX +251

Email pea.info@pea.gov.et

Addis Ababa

Ethiopia

Address

Addis Ababa Kadco Group building #2 From 7th to 8th floor. Ethio china Friendship Avenue around Wello sefere.