በነዳጅ ዘርፉ የሚስተዋል ሕገ-ወጥነትን ለመከላከል የነዳጅ ኩባኒያዎች በስራቸው ከሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች ጋር ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡
አዲስ አባበ፤የካቲት27/2017 (ነ.ኢ.ባ)
በነዳጅ ዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት የነዳጅ አከፋፋይ ኩባኒያዎች በስራቸው ከሚገኙ ማደያዎች ጋር ተወያይተው ሪፖርት እንዲያደርጉ በተሰጠው አቅጣጫ መሠረት ኩባኒያዎቹ ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ በዚሁ መሠረት በዛሬው ዕለት ኦላ ኢነርጂ ኢትዮጵያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባኒያ በስሩ ከሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎች ጋር ውይይት አድርጓል፡፡
የኩባኒያው ጀነራል ማናጀር የሱፍ ኢልሃሚሊ በውይይቱ ላይ በመገኘት ባደረጉት ንግግር በኩባኒያው ስር የሚገኙ ሁሉም ማደያዎች የሀገሪቱ የቁጥጥር ሕግ በሚያዘው መሠረት ስራቸውን እንዲሰሩ እና ንፁህ፤ጥራት ያለውና አስተማማኝ አገልግሎት በመስጠት ኩባኒያው የገነባውን ብራንድና ስም የማስጠበቅ ኃላፊነት እንዳለባቸው በማሳሳብ በኩባኒያው በኩል አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ገልፀዋል፡፡ ለዚህም ማሳሰቢያ ተግባራዊነት ሁሉንም ማደያዎች ቃል እንዲገቡ አድረገዋል፡፡
በውይይቱ ላይ ተገኝተው ማብራሪያ የሰጡት የባለስልጣን መ/ቤቱ የነዳጅ ዘርፍ ኃላፊና ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዲባራ ፉፋ እንደገለፁት የነዳጅ ግብይት ላይ የሚስተዋሉት ሕገ-ወጥ ተግባራት ዕለት ዕለት መልካቸውን እየቀያየሩና እየተባባሱ የመጡ በመሆኑ ህብረተሰቡን የኑሮ ጫና እንዲሸከም በማድረግ ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡ በነዳጅ ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ቀጥታ ህብረተሰብ ላይ የሚፈፀሙ በደሎች በመሆናቸው ሁሉም በኃላፊነት ስሜት ከችግሩ ለመውጣት የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንደሚገባው አሳስበው ወደ እርምጃ ከመገባቱ በፊት ውይይትን ማስቀደም እና መፍትሄ መስጠት ላይ ለማተኮር ሲባል እንደዚህ አይነት ውይይቶች እንዲደረጉ ቅድሚያ ተሰጥቷል ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል፡፡
በማደያዎቹ በኩልም ከነዳጅ አቅርቦት ፍትሃዊነት፣ዲጂታል ግብይት ላይ የሕብረተሰቡ ግንዛቤ አነስተኛ መሆንና ተባባሪ አለመሆን እና በጀሪካን እና በርሜል ሽያጭ እንድንፈፅም በደብዳቤ የምንታዘዝ በመሆኑ በኛም ስራ ላይ በበርሜል ተቀድተው በከፍተኛ ዋጋ በሕገወጥ የሚቸረቸር ነዳጅ የአቅርቦት ችግር እየፈጠረብን ነው ብለዋል፡፡
በኩባኒያው ኦፕሬሽን ዳይሬክተር አቶ ኃይሉ በሰጡት አቅጣጫ ሁሉም ማደያዎች ሽያጫቸውን ሙሉ በሙሉ በዲጂታል ማድረግ እንደሚገባቸው ከማንኛውም ሕገ-ወጥ ተግባር ራሳቸውን መጠበቅ እንደሚገባ እና የማሽን ብልሽትን በወቅቱ ማሳወቅና ማስጠገን እንደሚገባ የነዳጅ ትዕዛዝን በተመለከተ የማንም ጣልቃ-ገብነት ሳይኖር ከፍለው ባዘዙት መሠረት እንደሚቀርብ አረጋግጠዋል፡፡
|