ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ የከፍታ ዘመን ብሥራት፤ለብሔራዊ አንድነታችን፤ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ!
|
“ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ የከፍታ ዘመን ብሥራት፤ለብሔራዊ አንድነታችን፤ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ!” 18ኛው የብሔራዊ ሠንደቅ ዓላማ ቀን በባለስልጣን መ/ቤቱ ተከብሮ የዋለ ሲሆን በአከባበሩ ሥነስርዓት ላይ ኢነርጂ ዘርፍን የሚመሩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ባህሩ ኦሊጂራ ለሠራተኞች መልዕክት በማስተላለፍ እና በጋራ የኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር በመዘመር ሥነ-ስርዓቱ ተከናውኗል፡፡ አቶ ባሕሩ ዕለቱን በማስመልከት ባስተላለፉት መልዕክት ይህን የባንዲራ ቀን የምናከብረው የሀገራችን ከፍታ ዘመን አመላካች የሆኑ ትልልቅ ፕሮጀክቶች የተመረቁበት ውቀት ላይ ሲሆን በተለይም የታላቁ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ እና የጋዝ ምርትን ማውጣት መጀመራችን ለኢነርጂው ዘርፍ ዕድገት የክፍታ ማብሠሪያ ጭምር ነው ብለዋል፡፡ የዕለቱ ሥነስርዓትም የኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር በጋራ በመዘመር ተጠናቋል፡፡ “ ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ አዲስ ዘመን ከፍታ!” |