Downloads & publications
ኢትዮጵያ በ2033 የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎችን ከ40% ወደ 80% ለማሳደግ ትልቅ እቅድ በመያዝ የትራንስፖርት ዘርፉን ለመለወጥ ተዘጋጅታለች።
|
ወደ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የሚደረግ ሽግግር ኢትዮጵያ በ2033 የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎችን ከ40% ወደ 80% ለማሳደግ ትልቅ እቅድ በመያዝ የትራንስፖርት ዘርፉን ለመለወጥ ተዘጋጅታለች። በሁዋዌ ቴክኖሎጂ እና የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በተዘጋጀው የአካታች ኢነርጂ ጉባኤ ወቅት የሀገሪቱን ቀጣይ የትራንስፖርት ዘርፉ በሚመራበት ስትራቴጂ ጋር በተያያዘ በነዳጅ የሚሰሩ ተሸከርካሪዎችን ለመቀነስ የተያዘውን ዕቅድ አስመልክተው ኢንጂነር ባህሩ ኦልጂራ የነዳጅና ኢነርጂ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ተወካይ በጉባኤው ላይ ባደረጉት ንግግር አብራርተዋል፡፡ የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪ ተጠቃሚዎችን ለማበራከት ከተዘጋጀው የታክስ ማበረታቻ ጎን ለጎን የኢትዮጵያ መንግስት ከጥር 2017 ጀምሮ በነዳጅ የሚሰሩ መኪና ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ ሙሉ በሙሉ ማገዱ የሚታወቅ ሲሆን እነዚህ ማበረታቻዎች ከውጪ የሚገቡትን ቀረጥ እና ለግል ቤት ቻርጀሮች ነፃ ማድረግ፣ ግለሰቦች እና የንግድ ድርጅቶች በኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎች ላይ ኢንቨስት እንዲያደርጉ የሚያበረታታ መሆኑም በንግግራቸው ተጠቁመዋል። በዚህ መነሻነትም በቀጣይ በዋና ዋና አውራ ጎዳናዎች በየ50 እና 120 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በፍጥነት የሚሞሉ የህዝብ ሃይል መሙያ ጣቢያዎች የሚገጠሙበት ሀገር አቀፍ የኃይል መሙያ ኔትወርክ መዘርጋት የሚያስችል አሰራርን ዕውን ማድረግ ዓላማን ተከትሎ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ የሚመራው አዲስ በወጣው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ሃይል መሙያ ስርዓት (EVCS) መመሪያ ቁጥር 1034/2024 ሲሆን የፍቃድ መስፈርቶችን፣ የቴክኒክ ደረጃዎችን እና የኤሌክትሪክ ኃይል መሙያ አገልግሎት ሰጪ ማዕከላት የደህንነት ደረጃዎችን እንደሚዘረዝር ተነግሯል። ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪ መሠረተ ልማቷን በማሳደግ ረገድ መንግሥት በአገር አቀፍ ደረጃ በያዘው ዕቅድ 2,230 የኃይል መሙያ ጣቢያዎች እንዲኖሩ በማሳደግ አገልግሎቱ ለሁሉም ዜጎች ተደራሽነትን እንዲኖረው ለማድረግ ያለመ ነው። ይህ ተነሳሽነት ለነዳጅ የሚወጣን በቢሊዮን የሚቆጠር የውጭ ምንዛሪ ለመቆጠብ፣ የሀገሪቱን የካርበን ልቀት መጠን በመቀነስ እና ወደ ታዳሽ የኃይል ምንጮች በማሸጋገር የኢነርጂ ደህንነትን ያጎለብታል ተብሎ ይጠበቃል። በተጨማሪም ስትራቴጂው አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን (አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን) ከኤሌክትሪክ ተሸከርካሪ ጋር በተያያዙ አገልግሎቶች ውስጥ እንዲሳተፉ በማድረግ በሺዎች የሚቆጠሩ ስራዎችን በአዳዲስ ዘርፎች በማፍራት እና የኤሌክትሪክ አገልግሎቶች ተወዳዳሪ የኢንዱስትሪ ማዕከል በማቋቋም ኢኮኖሚያዊ ማካተት ላይ አፅንዖት ይሰጣል ተብሏል። የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን የኢነርጂ ደንቦችን ከትራንስፖርት ፖሊሲዎች ጋር አጣጥሞ በማውጣት ከትራንስፖርት ሚኒስቴርና በባለስልጣኑ መካከል ያለውን ትብብር በማጎልበት የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪ ስትራቴጂ በተሳካ ሁኔታ እንዲተገበር ቁልፍ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። ኢትዮጵያ ለዚህ ዘርፍ ያሳየችው ቁርጠኝነት ሀገሪቱን በአፍሪካ የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪ አገልግሎትን በመሪነት በማስቀመጥ ሀገሪቱ ለምትከተለው አረንጓዴ እስትራቴጂ ትልቅ እርምጃ ነው የተባለ ሲሆን ሀገሪቱ ለዚህ ሽግግር ስታዘጋጅ ባለድርሻ አካላት ለዘርፉ ከሚጠበቀው ፈጠራና እድገት ያላቸውን እምቅ አቅም ተጠቅመው እንደሚሰሩ ዕሙን ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡ |
ባለስልጣን መ/ቤቱ ብሔራዊ ኢነርጂ ብቃትና ቁጠባ ስትራቴጂን ለመተግበር ከተሰጠው ኃላፊነት በመነሳት የተለያዩ ፕሮግራሞችን ቀርፆ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል
|
ባለስልጣን መ/ቤቱ ብሔራዊ ኢነርጂ ብቃትና ቁጠባ ስትራቴጂን ለመተግበር ከተሰጠው ኃላፊነት በመነሳት የተለያዩ ፕሮግራሞችን ቀርፆ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ ከነዚህ ፕሮግራሞች አንዱ በከፍተኛ ኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ኢንዱስትሪዎች ላይ የሚተገበር የኢነርጂ አጠቃቀም ብቃትና ቁጠባ ኢነርጂ ኦዲት ፕሮግራም ነው፡፡ በዚህ ፕሮግራም ትገበራ የኢንደስትሪዎችን የኢነርጂ አጠቃቀም ብቃት ለማሻሻል የተለያዩ ስራዎች እየተሠሩ ሲሆን ከነዚህ መካከል ከከፍተኛ ኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚዎች ጋር የሚደረግ የፈቃደኝነት ኢነርጂ ማኔጅመንት ስምምነት ማደረግ፣በኢንደስትሪዎቹ ሊሚሠሩ ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠት እና ኢነርጂ ኦዲት ሥራዎችን ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡ በቀጣይም ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ጋር በጋራ በመሆን በዘርፉ የተጠኑ ጥናቶችን መሠረት በማድረግ በአምራች ኢንዱስትሪዎች ላይ የሚባክን ኢነርጂን ለማስቀረት የሚያስችሉ ሥራዎችን ለመስራት ቅድመዝግጅት እየተደረገ ይገኛል፡፡ |
ባለፈው ሣምንት የአፍሪካ ርዕሰ መዲና በሆነችው የኛዋ አዲስ አበባ 2ኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ ሲካሄድ ሰንብቷል፡፡
|
ባለፈው ሣምንት የአፍሪካ ርዕሰ መዲና በሆነችው የኛዋ አዲስ አበባ 2ኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ ሲካሄድ ሰንብቷል፡፡ በዚህ ጉባኤ የባለስልጣን መ/ቤቱ ኢነርጂ ዘርፍ ባለሙያዎችና ኃላፊዎች ተሣታፊ የሆኑባቸው መድረኮች ተካሂደዋል፡፡ በነዚህ መድረኮች ውይይት ከተካሄደባቸው ርዕሰ ጉዳዮች መካከል የኢነርጂ ተደራሽነት እና የመሠረተልማት ዝርጋታ በሚል ርዕስ በ children's investment fund foundation ፓቪሊዮን የተካሄደው ፓናል ውይይት አንዱ ነበር፡፡ በዚህ መድረክ ባለስልጣን መ/ቤቱን ወክለው አቶ ባህሩ ኦልጂራ የኤሌክትሪክ አቅርቦትና ሥርጭት ቁጥጥር መሪ ሥራ አስፈፃሚ በውይይቱ መክፈቻ ላይ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ በመልዕክታቸውም በዋነኝነት በአህጉሪቱ ለአየርንብረት መበከል ከሚጠቀሱ ምክንያቶች አንዱ ከትራንስፖርት ዘርፉ የሚመነጭ በካይ ጋዝ ልቀት መሆኑን አንስተው አፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥን ለመግታት አማራጭ ብላ ለያዘችው ንፁህ፣አካታችና ዘላቂ የኢነርጂ ሽግግር አፋጣኝ መፍትሄ እንደሚያስፈልገው ጠቁመዋል፡፡ ኢትዮጵያ ከምታመነጨው የኤሌክትሪክ ኃይል 95 በመቶ የታዳሽ ሃይል ምንጭ መሆኑን የሚጠቀስ ነው ያሉት አቶ ባህሩ አገሪቱ በትራንስፖርት ዘርፍ ብሔራዊ ኤሌክትሪክ ተሸከርካሪ ፕሮግራም ይፋ ማድረጓን ተከትሎ ኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎች አገልግሎት ላይ እየዋሉ ከመሆኑ ጋር በተገናኘ ተሸከርካሪዎቹ ኃይል የሚሞሉት ኢትዮጵያ ከምታመነጨው ታዳሽ ሃይል የመነጨ ነው ብለዋል፡፡ የትራንስፖርት ዘርፉን በኤሌክትሪክ አማራጭ መቀየር ነዳጅን ከመተካት ያለፈ ጠቀሜታ አለው ያሉ ሲሆን ይህም ማለት በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሞሉ የተሸከርካሪ ባትሪዎች ኤሌክትሪክን የማካማቻ አማራጭ ተደርገው ሊወሰዱ እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያም ለዚህ ምቹ መሠረተልማት እያዘጋጀች ትገኛለች ብለዋል፡፡ ይሁን እንጂ ይህን ራዕይ ለማሣካት ከፍተኛ ኢንቨስትመንት እንደሚጠይቅ ገልጸው ኢትዮጵያ በዚህ ዘርፍ ከፍተኛ የገበያ ዕድል ያላት መሆኑን አለምአቀፍና የአፍሪካ ባለሀብቶች እንዲያዩ ጋብዘዋል፡፡ ለዚህም እንደማሳያነት የአሁጉሪቱን ከፍተኛ ቁጥር ያለው ወጣት የሰው ሃይል ያላት ከመሆኑ ባሻገር ንፁህና ታዳሽ በሆነ የኃይል ምንጭ የበለፀገችና ለዘርፉ ምቹ ፖሊሲ ያላት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ፓናል ውይይቱም በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ የቀጠናው ሀገራት ትብብር፣የፋይናንስ ማፈላላግ እና የግል ዘርፉ ሚና ሊያሳድጉ የሚችሉ የንግድ ሞዴሎች ማዘጋጀት ያላቸውን አስተዋዕጾ ትኩረት እንደሚያደርግ አንስተዋል፡፡ አያይዘውም አፍሪካ በዓለማችን እየተከሠተ ላላው ለአየርንብርት ቀውስ ምክንያት ባትሆንም የመፍትሄ ሃሳቦችን ለማመንጨትና ለመወሰን ግን ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል፡፡ በንግግራቸው ማጠቃለያም የፓናሉ ተሣታፊዎች የአየር ንብረት ብክለትን ለመከላከል ኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎች ያላቸውን አቅም ለመጠቀም የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር ላይ ትኩረት መስጠት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል፡፡ |
More Articles ...
Page 1 of 4