በዓለም ባንክ ኢነርጂ ፖርት ፎሊዬ አስተዳደር ስር ከሚገኘው Prime Project ቡድን አባላት ጋር ውይይት ተደርጓል፡፡

 

መስከረም 8/2018 ዓ.ም(ነ.ኢ.ባ)

አዲስ አበባ

በዓለም ባንክ ኢነርጂ ፖርት ፎሊዬ አስተዳደር ስር ከሚገኘው Prime Project (Power sector reform investment and modernization in Ethiopia) ቡድን አባላት ከባለስልጣን መ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ደስታው መኳንንት (ዶ/ር) እና ከፕራይም ፕሮጀክት ቴክኒክ ቡድን ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

ከቡድኑ ጋር በተደረገ ውይይት በዋነኝነት በባንኩ በኩል በኢነርጂ ዘርፍ የሬጉላተሪ ስራዎችን ለማጠናከር ሊደረጉ ስለሚገባቸው ድጋፎችና በትብብር ሊሰሩ ስለሚቻልባቸው ጉዳዮች የሃሳብ ልውውጥ ተደርጎል፡፡

በባለስልጣን መ/ቤቱ በኩል ፕራይም ፕሮጀክትን ጨምሮ ተቋሙ ባአጠቃለይ በሚያከናውናቸው ሥራዎች ሊደረጉ ስለሚገባቸው የአቅም ግንባታና የሎጂስቲክ ድጋፎች በተመለከተ በተነሱ ነጥቦች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡ ባአጠቃላይ በባንኩና በተቋሙ መካከል ለወደፊቱ የሚሰሩ ሥራዎችን በተመለከተ ፍሬያማ ውይይት እንደተደረገ የውይይቱ ተሳታፊዎች ተናግረዋል፡፡