የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ አካሂዷል።
|
የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ አካሂዷል። አዲስ አበባ ጥቅምት 4/2018 ዓ.ም የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በዘርፉ በ2018 በጀት ዓመት በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ውይይት ተካሄደ። በውይይት መድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) በ2018 በጀት ዓመት በ1ኛው ሩብ ዓመት በዘርፉ የተከናወኑ ስራዎች በተመለከተ ዋና ዋና የትኩረት መስኳች ላይ የነበሩ አፈፃፀሞች ላይ የታዩ ጥንካሬዎች እና በክፍተት የታዩ ጠንካራ ጎኖች ዳካማ ጎኖችን ለማረም አላማ ያደረገ መድረክ መሆኑን ገልጸዋል። ሚኒስትሩ በንግግራቸው ካነሷቸው ነጥቦች መካከል ሀገር አቀፍ የንግድ ምዝገባና ኢንስፔክሽን አፈፃፀም ፣የውጭ ንግድ አፈፃፀም ከፍተኛ መሆን ፣2ኛው የንግድ ሳምንት ኤግዝቢሺንና ባዛር ከባለፈው ዓመት የንግድ ሳምንት ለየት ባለ ጥራት የተዘጋጀና ልምድ የተቀመረበት መሆኑ እንዲሁም የአለም ንግድ ድርጅት አባልነት ድርድር በተሳካ ሁኔታ የተካሄደበት፣ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ንግድ የተጀመረበት መሆኑን በጥንካሬ የተነሱ ነጥቦች ነበሩ። በሌላ በኩል በሩብ ዓመቱ በጥራት መንደር የሚሰጡ የወጪና ገቢ ምርቶች ፍተሻ እንዲሁም የገበያና ፋብሪካ ምርቶች ኢንስፔክሽን የተሻለ ስራዎች የተከናወኑ ቢሆንም በላብራቶሪና ቢሮ ግንባታ ፕሮጀክት ክትትል ላይ ክፍተቶች መስተዋላቸውን ገልጸዋል። |