የነዳጅ ውጤቶች የገበያ ድርሻ ቀመር ክለሳ ጥናት ለነዳጅ አከፋፋይ ኩባኒያዎች ቀረበ

 

የነዳጅ ውጤቶች የገበያ ድርሻ ቀመር ክለሳ ጥናት እና የገበያ ድርሻ ውሳኔውን ለማስፈጸም የሚያስችል ጋይድላይን ለነዳጅ አከፋፋይ ኩባኒያዎች ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

ቀደም ሲል ለነዳጅ አከፋፋይ ኩባኒያዎች የነዳጅ አቅርቦት ድርሻ የተለያዩ መስፈርቶችን መነሻ በማድረግ ሲሰራ የነበረ ሲሆን የዚህ ክለሳ ጥናት ግን በዘርፉ ያሉ ችግሮችን በማጥናት ከተለዩ ከችግሮች አንዱ መንስኤ አንዱ የገበያ ድርሻ አሰጣጥ ሆኖ መገኘቱ ሲሰራበት የቆየን ቀመር መከለስ በማስፈለጉ የተዘጋጀ መሆኑ ታውቋል፡፡

ከቀረበው ጥናት ለመረዳት እንደተቻለው በጥናቱ መሠረት የተከለሰው ገበያ ድርሻ ቀመር የነዳጅ አቅርቦትን ከማሻሻል ጎን ለጎን ፍትሃዊ ተደራሽነትን ባረጋገጠ መንገድ ምርቱን በቁጠባና ውጤታማነት መርህ መጠቀም የሚያስፈልግ በመሆኑ እንደሆ አመላክቷል፡፡

በውይይቱ መክፈቻ ላይ የባለስልጣን መ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ደስታው መኳንንት (ዶ/ር) በነዳጅ ግብይት ላይ ሲስተዋሉ የቆዩ ችግሮችን በዳሰሰ ንግግራቸው ከናሷቸው ነጥቦች መካከል በነዳጅ ግብይት በርካታ ተዋኒያኖች እንዳሉ ከነዚህ አካላት ጋር በተያያዘ የሚነሱ ችግሮች ገበያውን እየረበሸ እንደሚገኝ ማሳያዎችን በየደረጃው ያቀረቡ ሲሆን ባለስልጣኑም እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ጥናት ማድረጉን፤ ጥናቱን መሠረት ተደርጎ በተደጋጋሚ ከግብይቱ ተዋኒያን ጋር ውይይት መደረጉን ተናግረው የጎላ ጥፋት በተገኘባቸው አካላት ላይ ሕጋዊ እርምጃዎች መወሰዳቸውን በዝርዝር አብራርተዋል፡፡

አያይዘውም ዛሬ ለውይይት የቀረበው የገበያ ድርሻ ቀመር ማስተካከያ ክለሳ በዘርፉ ሲስተዋሉ የነበሩ ችግሮችን በከፊል ይፈታዋል ተብሎ የታሰበ መሆኑን የገለጹ ሲሆን በቀጣይ ውሳኔ ተሰጥቶበት ተግባራዊ የሚደረግ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊ ኩባኒያዎችም በሰጡት አስተያት የገበያ ድርሻ ቀመር ክለሳን በተመለከተ በተደጋጋሚ ሲያነሱት የነበረ ጥያቄ መሆኑን አንስተው ጥናቱ ላይ መካተት ነበረባቸው ያላቸውን ጉዳዮች እንዲሁም በመስፈርቶች ላይ ቢታዩ አፈጻጸም ላይ ችግር ሊፈጥሩ ይችላሉ ያሏቸውን ነጥቦች እንዲብራሩላቸው ጠይቀዋል፡፡

ለቀረቡት ጥያቄዎችና ለተሰጡት አስተያየቶች በተሰጠ ምላሽ የባለስልጣን መ/ቤቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ዲባራ ፉፋ በሰጡት ምላሽ መንግስት ነዳጅን ለህብረተሰቡ ለማቅረብ በከፍተኛ ደረጃ እያደረገ ያለውን ጥረት ሁሉም አካላት በቅንንት ሀገርን ማገልግል በሚል መርህ መተግበር እንዳለባቸው አሳስበው የገበያ ድርሻ ቀመሩ በጥናት ላይ ተመስርቶ የተሠራ በዚህ ሂደት ውስጥ የታዩ አሳሳቢ ህገወጥነቶች እየታዩ መሆናቸውን ጥናቱ በግልጽ ያሳየ መሆኑ ከዚህ በኋላ ነዳጅን በማሰራጨት ሂደት በሚፈጠሙ ጥፋቶች ጥብቅ ክትትል የሚደረግ እንደሆነ አሳስበዋል፡፡

በማጠቃለያው በዋና ዳይሬክተሩ እንደተገለጸው ጥናቱ ሲሰራ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅትን ጨምሮ ከተለያዩ አካላት መረጃዎች የተሰበሰቡ መሆኑን ገልጸው ጥናቱ ትኩረት አድርጎ የሠራውም ግልጸኝነት ባለው መንግድ ሕብረተሰቡን በዋነኝነት ተጠቃሚ ሊያደርጉ በሚችሉ መስፈርቶች ላይ በማተኮር እንደሆነ ተናግረዋል፡፡