354 የነዳጅ ማደያዎች ላይ ክስ ሊመሠረት ነው፡፡

 

ሐምሌ 5/2017 ዓ.ም (ነ.ኢ.ባ)

የነዳጅና ኢነርጅ ባለስልጣን ባደረገው ማጣራት ባለፉት ሶስት ወራት ነዳጅ በሕገ-ወጥ መንገድ ከዲጅታል ሽያጭ ውጭ በመፈፀም ከፍተኛ መጠን ያለው ነዳጅ ላልተገባ ተግባር እንዲውል በማድረጋቸው 526 ማደያዎች የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ቢሰጣቸውም ከነዚህ ውስጥ 354 ማደያዎች ከሕገ-ወጥ ድርጊታቸው ስላልታረሙ በአዋጁ በተቀመጠው መሰረት ማደያዎቹ ባሉበት ክልል ንግድና ግብይት ቢሮ በኩል ክስ እንዲመሰረትባቸው እና ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸው የነዳጅና ኢነርጅ ባለስልጣን ትዕዛዝ አስተላልፏል።

የነዳጅ አከፋፋይ ማደያዎች በነዳጅ ግብይትና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1363/17 የተደነገጉ የግብይት አሰራሮችን አክብረው እንዲሰሩ የሚገደዱ ቢሆንም እነዚህ ማደያዎች ይህን ድንጋጌ ቸል ብለው ከሕግ ውጪ ሲሲሩ በመገኘታቸው ውሳኔ መተላለፉን ባለስልጣን መ/ቤቱ ያወጣው የክስ ትዕዛዝ ያመለክታል፡፡

ሀገሪቱ በብዙ ድካምና ጥረት የምታገኘውን የውጭ ምንዛሬ መንግስት ለነዳጅ ግዥ ቅድሚያ በመስጠት በከፍተኛ መጠን ያለው የውጭ ምንዛሬ ወደ ሀገር ውስጥ የሚያስገባውን ነዳጅ በየደረጃው የሚገኙ የነዳጅ ግብይት ተዋናይ በተለይም የነዳጅ ማጓጓዣ ቦቴ ባለንብረቶች፥ አቅራቢ ኩባንያዎች እና ማደያዎች በከፍተኛ ጥንቃቄ ኃላፊነታቸውን መወጣት እንዳለባቸው እና ግዴታቸውን በማይወጡት ላይ ጥብቅ እርምጃ እንዲወሰድ የነዳጅ ግብይትን ለመቆጣጠር በወጣው አዋጅ ቁጥር 1363/17 መደንገጉ ይታወቃል፡፡

በዚሁ መሠረት የነዳጅና ኢነርጅ ባለስልጣን በነዳጅ አቅርቦትና ግብይት ድርሻ ያላቸው አካላት ሕግና ስርአትን አክብረው እንዲሰሩ እያሳሰበ የክትትልና ቁጥጥር ስራውን በማጠናከር ከሕገ-ወጥ ድርጊታቸው የማይታረሙትን የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳውቋል።
 
  • Hits: 3950

Contact Us

Petroleum and Energy Authority 

P.O.BOX 2554

Tel +251 

FAX +251

Email pea.info@pea.gov.et

Addis Ababa

Ethiopia

Address

Addis Ababa Kadco Group building #2 From 7th to 8th floor. Ethio china Friendship Avenue around Wello sefere.