ደስታው መኳንንት (ዶ/ር) ከሚያዚያ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሁነው በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ተሹመዋል።

 

ሚያዚያ 25 ቀን 2017 ዓ/ም

የነዳጅና ኢርጂ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ደስታው መኳንንት (ዶ/ር) ከሚያዚያ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሁነው በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ተሹመዋል።

ክብርት ወ/ሮ ሠሀርላ አብዱላሂ ከመጋቢት 2014 ዓ.ም ጀምሮ የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን መሥሪያ ቤትን ዋና ዳይሬክተር በመሆን ላለፉት ሦስት ዓመታት ሲመሩ የቆዩ መሆኑ ይታወቃል።

በቆይታቸውም':-

  • የነዳጅ አቅርቦት፣ ሰርጭትና ግብይት ሥርዓት ተገቢ ቁጥጥር እንዲደረግበት
  • የቴክኖሎጂ አማራጮችን መጠቀም እንዲቻል በማድረግ ፣
  • ዲጅታል የነዳጅ ግብይት ወደ ስራ በማስገባት፣
  • የታለመ የነዳጅ ድጎማ ስርአትን

በማስፈፀም በኩል ላደረጉት ቀና አመራርና አስተዋፅዖ ምስጋናችን እያቀረብን፤ መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው እንመኛለን።

በምትካቸው በዋና ዳይሬክተርነት ለተሾሙት የቀድሞው የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ኢርጂ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ደስታው መኳንንት (ዶ/ር) መልካም የስራ ዘመን እንዲሆን መልካም ምኞታችንን እንገልፃለን።

 

 

 

Contact Us

Petroleum and Energy Authority 

P.O.BOX 2554

Tel +251 

FAX +251

Email pea.info@pea.gov.et

Addis Ababa

Ethiopia

Address

Addis Ababa Kadco Group building #2 From 7th to 8th floor. Ethio china Friendship Avenue around Wello sefere.